ፅሁፎች

ብአዴን ስሙን ሲቀይር…| ውብሸት ሙላት

ንቅናቄ ፣ ግንባር እና ፓርቲ (ድርጅት)? (ብአዴን ስሙን ሲቀይር…) ዉብሸት ሙላት የተቃዋሚ (የተፎካካሪ) ፓርቲዎችን ትተን አገሪቱን በክልልም ሆነ በፌደራል ደረጃ እያስተዳሩ ያሉትን ፓርቲዎች አደረጃጀት ስናጤን አንድ ግር የሚል ነገር ማስተዋላችን አይቀርም፡፡ እሱም የተወሰኑት ግንባር (ሕወሃት/TPLF፣ኢሐአዴግ)፣ሌሎቹ ንቅናቄ (ብአዴን፣ደሕዴን፣ጋህዴን) ፣ የተወሰኑት ፓርቲ (አብዴፓ፣ ሶሕዴፓ፣ ቤጉደፓ)፣ቀሪዎቹ ደግሞ ድርጅት (አህዴድ) የሚል ገላጭ ወይም አመላካች መጠቀማቸው ነው፡፡ ሕወሃት (TPLF)አንድ ድርጅት ብቻ ሆኖ ሳለ በግንባርነት መጠራቱ ...

Read More »

ከጋላነት ወደ ኦሮሞነት ለምን? | በደብተራው ፀጋዬ

“If you can’t stand the heat get out of the kitchen” የዘመናችን ጋላዎች ጋላ አትበሉን ስማችን ኦሮሞ ነው ይላሉ። ይህን ትርክት ተቀብሎ አብዛኛው ሰው ጋላን በስያሜው መጥራት አቁሞ ኦሮሞ እያለ ይጠራል። በታሪክ የአማራን እና የደቡብ ኢትዮጵያን መሬት በ16ኛው ክፍለ ዘመን በወረራ የያዘው ማነው? ጋላ አይደለምን? ኦሮሞ ወረረ የሚል አንድም ቦታ አልሰፈረም። የውጭ እና የሀገር ውስጥ ፀሐፊዎችም ጋላ የሚባል ህዝብ በነባሩ ...

Read More »

የዛሬው ራያ፤ የቀድሞው አንጎት አውራጃ እስከ አሸንጌ ሐይቅ ድረስ የወሎ ክፍል እንጂ የትግራይ ….

የዛሬው ራያ፤ የቀድሞው አንጎት አውራጃ እስከ አሸንጌ ሐይቅ ድረስ የወሎ ክፍል እንጂ የትግራይ አካል አይደለም፤ አልነበረምም! (አቻምየለህ ታምሩ) በቤተ ወያኔ መቼም እሳ ብሎ ነገር የለም። ጊዜ የሰጠው ቅል ድንጋይ ቢሰብር፤ ፋሽስታዊ አገዛዛቸውን የዘላለም ርስት አድርገውት ከተግባራዊነቱ በመለስ ምንም ያልቀረውን የአገራቸውን የታላቋ ትግራይ ሪፑብሊክን ደቡባዊ ድንበር አሸንጌን አልፈው አንጎትን [ሰሜን ወሎን] ዘልቀው እስከ አለውሀ ድረስ ለማማተር ይቃጣቸዋል። ካለፉት ሁለት ወራት ወዲህ ...

Read More »

ለጡረታ የተጠጋው የአንድነቱ ፖለቲካ እና የአማራ ህዝብ የህልውና ትግል

(ሺሀሳብ አበራ) የኢትዮጵያ ተፈጥሮ ብሄር ነው፡፡ ተወደደም ተጠላ ከብሄርተኝነት ማምለጥ መሬትን ተኩሶ እንደመሳት ይቆጠራል፡፡ ማምለጥ አይቻለም፡፡ ወንድሜ መልካሙ ተሾመ በኢትዮጵያ ሰማይ ስር ብሄርተኝነትን ማውገዝም ሆነ ኢትዮጵያዊነትን መቃረን እኩል አደገኞች ናቸው ይላል፡፡ ልክነቱ ሚዛን ይደፋል፡፡ ብሄርተኝነት እንደ ጎሰኝነት የሚመለከቱትም ሆነ፣ ኢትዮጵያዊነትን እንደ አውሬ የሚመለኩት ከገሃዱ ዓለም የራቁ ናቸው፡፡ አንዱን ጥሎ፣ ሌላውን አንጠልጥሎ ማሸነፍ አይቻልም፡፡ … ከ 1966 ጀምሮ ሲዋልል ከርሞ አሁን ...

Read More »

አቶ ደመቀ መኮንንን ለሱዳን መሬት ሸጠ ብሎ ያስወራው ሰው፣ እና ሊታሠሩ የነበሩት ሦስቱ ባለሥልጣናት

(ሞረሽ፣ ከብአዴን ቤት) ሀ. ደመቀ መኮንንን መሬት ሽጧል ባዩ፤ነገሩ እንዲህ ነው፡፡ አቶ ደመቀ መኮንን የአማራ ክልል ምክትልና የአቅም ግንባታ ቢሮ ኃላፊ ነበር፡፡ ምክትል የቢሮ ኃላፊዎቹ ደግሞ አቶ ስማቸው ንጋቱና አቶ ደሳለኝ አምባው ነበሩ፡፡ አቶ ስማቸው ኋላ ላይ የክልሉ የገጠር ልማት (መንገድ?) ሃላፊ የነበረና አሁን ላይ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የግእዝ መምህር ነው፡፡ አቶ ደሳለኝ አምባው ከደመቀ ቀጥሎ አቅም ግንባታ ቢሮ ሐላፊ፣ ...

Read More »

ዋጃና ጥሙጋ -ራያ!

(የሱፍ ኢብራሂም) ———————— ትርክቱ እድሜ ጠገብ መሆኑ ይታወቃል። ይህ ቀጥሎ ትህነግ(ህወሀት) የደርግን አገዛዝና የአማራን ህዝብ አንድ አድርጋ በሳለችበት የተንሸዋረረ ምልከታ የደርግ አገዛዝ ሲወድቅ የአማራን ህዝብና ግዛቶች በመዝረፍ ለታላቋ ትግራይ ግብአት አዉላቸዉ ቆይታለች፣ አሁንም ቀጥሏል። ነገር ግን ከአሁን በኋላ ረጅም እድሜ ሊኖረዉ አይችልም። የአማራ ህዝብ ባለታሪክና ታላቅ ህዝብ በመሆኑ ሊሸነፍ የሚችል አይደለም። አማራን አሸንፈናል ያሉት ሁሉ የጊዜ ጉዳይ ሆኖ እንጂ ከመነሻዉ ...

Read More »

የአማራው “ብሔርተኛ” የሚያስፈልጉት ጥንቃቄዎች

(ጌታቸው ሽፈራው) 1) ትህነግ/ህወሓት የሚባል ነጭ ወርቅ የሚያፍስበት ወርቃዊት (ወልቃይት) እና ራያ እንዲነሳበት የማይፈልግ ጠላት አለው። ይህ የመጀመርያ መተዳደሪያው ደንቡን ሲፅፍ ጠላቱን አማራ ብሎ የጀመረ ድርጅት የአማራውን እንቅስቃሴ በክፉ አይን ከማየት አልፎ ለማጥፋት ወደኋላ የማይል ነው። 2) አማራው በሀገር ግንባታ የነበረውን አውንታዊ አስተዋፅኦ በአሉታዊነት እያነሳ፣ የአማራውን ብቻ መቀስቀሻ አድርጎ የኖረው የተገንጣይ ድርጅት ብዙ ነው። በአንድ ወቅት ከገዥዎች ጋር ሆኖ አማራው ...

Read More »

አቶ ንጉሱ ጥላሁን የአማራ ክልል ኮምንኬሽን ቢሮ ሃላፊ ለአቶ በረከት ስምኦን መልስ ሰጡ!!

(ከአቶ ንጉሱ ጥላሁን የአማራ ክልል የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሀላፊ) ሰሞኑን የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ አቶ በርከትን እና አቶ ታደሰን ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነታቸው ማገዱን ተከትሎ አቶ በረከት ለተለያዩ ሚዲያዎች ውሳኔው:- => በስብሰባው ለመታደም ዋስትና ስላልተሰጠኝ መገኘት አልቻልኩም፣ => ውሳኔው መሰረተ ቢስ ነው፣ => የኤርትራ መንግስት እጅ እና ፍላጎት ስለላበት በኤርትራ መንግስት ትዕዛዝ የተፈፀመ ነው፤ እኔ እርምጃ የተወሰደብኝ ኤርትራዊ ዘር ስላለኝ ነው፣ => ...

Read More »

የምንገነባው ብሔርተኝነት ግራዋ እንጂ ሚሪንዳ ስላለመሆኑ!

(ክርሥቲያን ታደለ ፀጋዬ–ገብርዬ) ***** በርካቶች አማራው በአማራነቱ ተደራጅቶ ይፋዊ የፖለቲካ ድርጅት ማቆሙን ተከትሎ ብዙ ብዙ ነገር ተናግረዋል። ብሔርተኝነቱን አገር አፍራሽ ካሉት እስከ ጦረኛ ቡድን ስለሆነ መፍረስ አለበት ባዮች ድረስ የስንት መደዴዎችን ድስኩር ሰምተናል፤ ማቀርሸታቸውንም አንብበናል። አንዳንዶች ይፋዊ ዛቻዎችን ሳይቀር በብሔርተኝነቱ አንቀሳቃሾች ላይ ሰንዝረው ታዝበናል። ወደ ተራ ብሽሽቅና ስም ማጥፋትም ገብተው አይተናል። ሁሉንም ግን ከመጤፍ ሳንቆጥር ዛሬም ከወጀቡ በላይ ከፍ ብለን ...

Read More »

እናዉቅላችኋለን አትበሉን – ለራሳችን እንበቃለን ! (ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ)

የኢትዮጵያን ፓለቲካ በቅርበት የሚያዉቅና የሚከታተል ሰዉ በግልጽ እንደሚረዳዉ ባለፉት ሁለት ዓመታት በኢትዮጵያ የፓለቲካ ምህዳር ዉስጥ ታላቅ የህዝብ ንቅናቄ ተፈጥሯል፡፡ ይህ የህዝብ ንቅናቄ በአማራ ህዝብ ዘንድ በተለምዶ ተቀባይ ተደርገዉ የሚወሰዱ ሙግቶችን ፣ መረዳቶችንና እምነቶችን እንደገና በማጤንና በማጠየቅ አዲስ ሙግት ፣ የፓለቲካ አረዳድና ሃሳብ ይዞ የመጣ ክስተት ነዉ፡፡ ይህ የ”አማራ ነን” – ሃሳብና የፓለቲካ ፍልስፍና ሲሆን አፈጣጠሩ ሸጋ የሆነ የአማራ ብሄርተኝነትንም ወልዷል፡፡ ...

Read More »

የአማራ ብሔርተኝነት የዚህ ወቅት የኢትዮጵያ ፖለቲካ መዘውር እና የጠንካራ ኢትዮጵያዊነት እና አገራዊ አንድነት መድህን

(በደሴ ጥላሁን አያሌው) 1. መነሻ ቁም ነገር፤ የአማራ ብሔርተኝነት በኢትዮጵያ “እርጅና ሊቃጣው የሚገባ በነበረው” የማንነትና የግራ ዘመም የፖለቲካ ልክፍት ታሪክ የረጅም ጊዜ “ታዛቢና በጥልቀት ገምጋሚ” ማንነትና የኢትዮጵያዊነት ካስማ ሆኖ ነው የከረመው፡፡ በዚህ ምክንያት በጭብጡ ዙሪያ ዳጎስ ያለ ሳይንሳዊ ምልከታ ለማቅረብ መሞከር ከባድ ነው የነበረው፡፡ ሆኖም ያለፉት ሦስት ዓመታት ለአማራ ህዝብ የአብርሆት (“Enlightenment”) ጊዚያት ነበሩ ማለት ይቻላል፡፡ ይሄው “የአማራ የአብርሆት ዘመን” ...

Read More »

ግዴላችሁም ያለንበት ሁኔታ ትንሽ “ረጋ” ማለትን ጠይቋል | ወንድይራድ  ሃ/ገብርዔል

“government comes and goes, State is forever” መንግስት ይመጣል መንግስት ይሄዳል ሃገር ግን ለዘላላም ይኖራል።  እዚህ ላይ State የሚለው ቃል ሃገር በሚለው አረዳድ መወሰድ ይኖረበታል። ለነገሩ ትክክለኛውም አረዳደ ይሄው ነው። State and Government (ሃገር እና መንግስት) የሚሉት አረዳዶች ብዥታ መፍጠራቸውን ስለማስብ ነው “ትክክለኛው አረዳድ” ስል ማስመርን የወደደኩት። State (ሃገር) በሚባለው አገላለጽ ውስጥ አራት መሰረታዊ ጉዳዮች ይኖራሉ። ህዝብ (the people)፡ የግዛት ...

Read More »

እውነታ እና ፖለቲካ በኢትዮጵያ – Gurbaa Anis Isinumarrati- | ወንድይራድ ሃ/ገብርዔል

                             Gurbaa Anis Isinumarrati!  “እኔም እኮ ከእናተው ነኝ  …  ይህንን የተናገሩት ግርማዊ ቀዳማዊ ሃይለስላሴ ንጉስተ ነገስት ዘ-ኢትዮጵያ ናቸው። አሌ የሚል ከመጣ የተከበሩ አቶ ቡልቻ ደመቅሳን በእማኝነት እንካችሁ ብለናል። የሚከተለው የምስክርነት ቃል የተወሰደው ከአቶ ቡልቻ ደመቅሳ አንደበት ነው። በነገራችን ላይ በዚህ አጋጣሚ ረዥም እድሜና ጤና ለአቶ ቡልቻ ደመቅሳ መመኘትን እወዳለሁ። አቶ ቡልቻ በአግባቡ ያልተነበቡ የታሪክ መጽሃፍ ናቸው። አቶ ቡልቻ ለሰራ አጋጣሚ ኒወዮርክ ...

Read More »

ጀዋር መሃመድ እና “የጉዲፈቻ” ፖለቲካ | ወንድይራድ ሃ/ግብረዔል

                                                              የምታገኘው የምታየውን ነው!  What you see is what you get!  ጀዋር መሃመድ ኢትዮጵያ ውስጥ ገብቶ መሬት ላይ እግሩ ሲረግጥ እያደረገ ያለው ነገር ሚኒሶታ አየር ላይ በነበረበት ጊዜ በድህረገፅ ሲነግረንና ...

Read More »

     የአቶ ንጉሱ ንግግር- ወንድይራድ ሃ/ገብርዔል | ከግዮን መገናኛብዙሃን ማዕከል GMC

“….የአማራ ህዝብ ወንድም ከሆነው የኦሮሞ ህዝብ ጋር በኦሮምያም በአማራም ተሰባጥሮ በመኖሩ ምክንያት …  (ይደገም! … ይደገም! … ይደገም! ሲል ታዳሚው በፍተኛ ድምጽ ጩህቱን አስተጋባ …. አቶ ንጉሱም ደገሙት!) … የአማራ ህዝብ ወንድም ከሆነው የኦሮሞ ህዝብ ጋር በኦሮምያም በአማራም ተዋህዶ … ተዋልዶ … ተጋምዶ የሚኖር ህዝብ በመሆኑ ይህንን ገመድ በማጥበቅ … አንድነትን በማጎልበት ታላቅ ሃላፊነት ይዞ የመጣ ሚዲያ መሆኑን በመገንዘብ የአማራ ...

Read More »