የአማራን ሕዝብ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ጥያቄዎች ለመመለስ ጠንካራ አንድነት መመሥረት እንደሚገባ ተገለጸ፡፡

ባሕር ዳር፡ ሰኔ 21/2011ዓ.ም

ዶክተር ጌቴ ዘለቀ ሰኔ 15 ቀን 2011ዓ.ም በአማራ ክልል የተከናወነውን አስመልክቶ ‹‹የችግሩ መፈጠር ሁሉንም ያሳዘነ ነው፤ ከችግሩ በኋላ ሕዝቡ የተፈጠረውን አጋጣሚ በሰከነ መንገድ ማየት የሚገባው ትልቅ የፈተና ወቅት ነው›› ብለዋል፡፡ የአንድ ሰው ጀግንነት የሚለካው ወደተጠመደበት ወጥመድ ባለመግባት ወይም ወጥመዱን ማፈራረስ በመቻል እንደሆነ  ተናግረው ሁላችንም ወጥመዱን ለማክሸፍ እንድንሰራ ጠይቀዋል ፡፡ ትናንት ፈተናዎች የነገ ራዕዮቻችንን ይዘው እንዳይጠፉ ግን ሁሉም የሚችለውን በማድረግ ለሀገሩ ብልፅግና ዋስትና መሆን እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

ፕሮፌሰር ዳንኤል ቅጣው ‹‹የተፈጠረውን ሐዘን እያራገፍን ከላዩ ላይ በመቆም ከስሜት በመውጣት መፍትሔዎችን ለማምጣት መሥራት ያለብን ወቅት ነው›› ብለዋል፡፡ ፕሮፌሰር ዳንኤል በሐዘኑ ‹ሌት ከቀን›

የAmhara Mass Media Agency ምስል

 እያሰቡ እና እየተጨነቁ መኖር መጪውንም ተስፋ አብሮ የሚያጠፋ በመሆኑ ሕዝቡ መረጋጋት እንደሚኖርበት ተናግረዋል፡፡

ዶክተር ገበያው ጥሩነህ ደግሞ ‹‹ድርጊቱ ያልተጠበቀ፣ ያስደነገጠ እና አንገት የሚያስደፋ ነው›› ብለዋል፡፡ ዶክተር ገበያው የተፈጠረውን ሐዘን እያሰቡ ባለመቆዘም ማለፍ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡የAmhara Mass Media Agency ምስል
ምሁሩ የአማራን ሕዝብ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ጥያቄዎች ለመመለስ ጠንካራ አንድነት የግድ መሆኑንም አብራርተዋል፡፡ ‹‹በአንድነት እና በጋራ ጥቅሞች ላይ ያልተመሠረተ አካሄድ የየትኛውንም የተናጠል መብት እና ፍላጎት አያሞላም›› ነው ያሉት፡፡

እንደዚህ ያሉ አጋጣሚዎች በበለጠ ቁጭት ለላቀ አንድነት እና ጥንካሬ መነሻ ሊሆኑ እንደሚገባ ያመላከቱት ዶክተር ገበያው የአማራ ምሁራን መማክርት በክልሉ ያሉ ቸግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት እንቅስቃሴ መጀመሩን አስታውቀዋል፡፡

አብመድ ያነጋገራቸው ሌሎች ምሁራን በበኩላቸው ‹‹ድርጊቱ የአማራ ሕዝብ አንድነት ቀናኢነቱን ሊያሳይ የሚገባው ወቅት እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡ የአማራ ሕዝብ የተፈጠረውን ችግር እንደወርቅ ተፈትኖ እንዲወደድ መልካም አጋጣሚ አድርጎ ሊወስድ እንደሚገባም መክረዋል፡፡

‹‹መፍትሔዎች የሚመጡት ከሰከረ አካሄድ ወጥቶ በሰከነ መንገድ ስሜትን በመቆጣጠር ነው›› ያሉት ምሁራኑ አሁን ላይ በስሜት መፍትሔ ማምጣት እንደማይቻል ልብ ማለት እንደሚገባ ነው ያመለከቱት፡፡

ከችግሩ ውስጥ ለመውጣት የሐሳብ ልዩነትን ለግቦች መሳካት እንደጥንቃቄ እና እንደመልካም አጋጣሚ በመቁጠር መተማመን ላይ የመድረስ ባሕል እንዲጎለብት አጋጣሚውን እንደመማሪያ መውሰድ እንደሚገባም ምሁራኑ አሳስበዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ግርማ ተጫነ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*

x

Check Also

ብዙ ጊዜ እውነትን ውሸት ይቀድመዋል-የሺሃሳብ አበራ

ብዙ ጊዜ እውነትን ውሸት ይቀድመዋል፡፡ እውነት ዳተኛ ናት ወይም ቶሎ አትገለፅም፡፡ እውነት ቶሎ መገለፅ ባለመቻሏ ምክንያት በዓለም ...