ስለፌስታል ከተነሳስ!- ረዳት ፕሮፌሰር በለጠ ሞላ

“አንዴ ባላደራ አንዴ ባልደራስ እያሉ የሞጋሳ ስም እያወጡ….” አዲሱ አረጋ ቂጥሳ ስለ እስክንድር ነጋ ከተናገረው ውስጥ….።

(ይህ ሰው በአአዩ የክፍል ጓደኛየ ነበር በቅርበትም እውቂያ ነበረን….ስናወጋም “ነፍጠኛ” ሲል ካንዴም ሁለቴ መተንኮሱን እሱ ቢረሳ እኔ የማልረሳ ነኝ። ይህ የሆነው ከ1995-1997 ዓ.ም ሲሆን ያኔ እሱ ፖለቲካል ሳይንስ ሲያጠና እኔም ፍልስፍና ሳጠና፣ የፖለቲካል ሳይንስ ትምህርትንም በMinor ስትሪም 8 ያህል የጥናት ኮርሶችን ስወስድ ሳለ ይህንኑም ተቀላቅለን በተማርንበት ግዜ ነው….ጥቁር ፌስታል ይወድ እንደነበር ግን እኔው ምስክር ነኝ። በጥቁር ፌስታልም ሁሌ ወደዩኒቨርሲቲ ግቢ ይዞት የሚገባው ነገር ነበር። ዛሬ ላይ ግን አላውቅም)!
—————
ለማንኛውም ይሄው ሰው “ሞጋሳ” ብሎ ጀግናውን እንደከሰሰው ሁሉ ስለ “ሞጋሳ” ከተነሳ አይቀር ….ሞጋሳ ማለት ስምንተኛው የጋዳ የሽግግር አመት ሲመጣ ተረኛው ጄሌ “ሆ!” እያለ ወደ አዲስ ግዛት የሚተምበት፣ በመንገዱም ላይ ያገኘውን ሁሉ “ኬኛ” እያለ የሌላው የሆነውን የሚወርበት፣ ህዝብንም በሞጋሳ ባህል ስር አውሎ “ከዛሬ ጀምሮ ኦሮሞ ነህ ብለናል ስለዚህ ኦሮሞ ነህ….ይህም ካልሆነ እልቂትህ ነው” በማለት የሌላውን ህዝብ ማንነቱን፣ ባህሉን፣ ታሪኩንና ቋንቋውን የሚውጥበት፣ የስልጣኔ አሻራውን የሚያጠፋበት፣ ግዛቶቹን ሁሉ በአዲስ የኦሮሞ ስም የሚሰይምበት ባህል ነው። Donald Levine….the Amhara thesis and the Oromo anti-thesis ብሎ በውስጠ ወይራ ያስረዳው ይህንኑ ተቃርኖአዊ የአለም ምልከታንና የታሪክ ግንኙነት ሲሆን አማራ ያቆመውን ሁሉ ይህኛው ጄሌ በሞጋሳ ባህል ስር አውሎ ሲያጠፋው መኖሩን በማስታወስ ነው።
————
የታሪክ ድርሳናት እንደሚያስታውሱን ከሆነ አማራው ክፉኛ ተዳክሞ በተገኘበት በ16ኛው ክፍለዘመን ላይ ቀዳሚው የሞጋሳ ዘማች ጄሌ “ሆ!” ብሎ ከመዳወላቡ ገና ሳይስፈነጠር የዛሬው አሩሲ ቢፍቁት አማራ ሲዳማና ሀድያ ነበር፣ ሸዋ የአማራ ደማቅ ማእከል ነበር፣ ንጉስ ገላውዴወስም በናዝሬት ሲወለድ ይህች የትውልድ መንደሩ የአባታዊ ግዛቱ ማእከላዊ ርስት እንጅ ደቡባዊ ጠረፍ አልነበረችም፣ ቢዛሞም ወለጋ ሳይባል የደመቀ አማራ ነበር፣ ዛሬ ላይ የኦሮሞን ፖለቲካ በበላይነት ከሚመሩት ከወለጋወቹ ተወላጆች ውስጥ ብዙወቹ አያትና ቅድም አያቶቻቸው የጎጃም አማሮች እንደሆኑ ሞቅ ሲላቸው የገለጡት ጉዳይ ነው፣ ጅማ የከፋው ጋኪ ሸረኮ አባታዊ ርስት ነበር፣ ኢሉባቦር የጋምቤላ ነበር፣ ሀረርጌም የአማራና የሶማሌ ነበር…..።

እነሆ ዛሬ ላይ “ሞጋሳ” በ”መደመር” ስም ተሸፋፍኖ ቄሮው ለሁለተኛ መስፈንጠር ያለውን ከፍተኛ ርሀብና አጠቃለይ አባዜውን እየታዘብን እንገኛለን። የቄሮው አለቃ ጃዋር መሀመድም ሲጠየቅ እንዳስታወቀው ምኞቱ የ16ኛው ክ/ዘመንን ኦሮሞ ማየት እንደሆነ ገልጧል (የዘመኑ አቆጣጠር ያው የአማራ ነው፣ የታሪኩ ክትበትም እንዲሁ የአማራ ነው፣ ጃዋርም ቢሆን ይህንን ታሪክ የተማረው አማራው ከትቦ ስላስቀረለት ነው)።
ታዲያ ይህን ፍላጎት ነቅተው የታዘቡ የወቅቱ የአማራ ጠባቂወች፣ የኢትዮጵያ ባላደራወች ይህንን ሁለተኛ የመስፈንጠር አደጋ አሽትተዋልና ነው “የዛሬ 500 አመት ግድም ገጥሞን ከነበረው ይልቅ የከፋ….” ሲሉ የተኛውን አማራ በመንደፍ ለማባነን የወደዱት።
የተኛችሁ ወዮላችሁ!
————————
መዝጊያ!
ይህ ዛሬ ላይ የምንታዘበው ሞጋሳዊ የመስፈንጠር ፍላጎትና የኬኛ ፖለቲካ በቀደሙት ዘመናት የኦሮሞ ህዝብ ጠቅላይ ባህል የነበረ ቢሆንም ዛሬ ላይ ግን ስክነትና ማስተዋልን ያጡት የኦሮሞ ልሂቃኖች ገደብ የለሽ ፍላጎትና መቅበዝበዝ እንጅ የሰፊው የኦሮሞ ህዝብ ፍላጎት አይደለም!
ዛሬ ላይ የኦሮሞ ህዝብ ልክ እንደማናቸውም የኢትዮጵያ ህዝቦች ሲጀምርም ሲጨርስም ፍላጎቱ ግልፅ ነው…..ፍላጎቱም ሰላም፣ ልማት፣ ፍትህ፣ እኩልነትና የሰብአዊ መብት መከበር ነው።
ልሂቃኑ ግን በእብደት ህዝቡን በዛሬው ዘመን ላይ አስቀምጦ እሱ መቶ አመቶችን ወደኋለ ተመልሶ ዳግም የታሪክ ግርጌ ላይ ለመቀመጥ ወዷል….ይህም የኋልዮሽ ጉዞውና ያልተገራ ፍላጎቱ ያጠፋዋል እንጅ አይጠቅመውም!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*

x

Check Also

ብዙ ጊዜ እውነትን ውሸት ይቀድመዋል-የሺሃሳብ አበራ

ብዙ ጊዜ እውነትን ውሸት ይቀድመዋል፡፡ እውነት ዳተኛ ናት ወይም ቶሎ አትገለፅም፡፡ እውነት ቶሎ መገለፅ ባለመቻሏ ምክንያት በዓለም ...