የአማራ ክልል ከፍተኛ የፀጥታ ክትትል ችግር አለበት – ሚኪ አማራ

⚡️ክልሉ እንደ ሃብታም ቤት ተበርግዶ (የሃብታም ቤትስ አንዳንዴ ይዘጋል) ሲፈልግ ከባድ መሳሪያ፤ ሲፈልግ ታንክ ፤ሲፈልግ የሰለጠነ ወታደር የሚገባበት የሚወጣበት ዝርዉ ቦታ መሆኑ የታወቀ ነዉ፡፡ ሀገሪቱ ዉስጥ እራሱ ህገወጥ የወታደር ማሰልጠኛ ካምፖች ያሉት አማራ ክልል ነዉ፡፡ በጣም እኮ ገራሚ ነገር ነዉ፡፡ወደ አማራ ክልል ከየትኛዉም አቅጣጫ ስትገባ ምንም አይነት ቁጥጥር የለም፡፡ በእርግጥ በአንዲት ሀገር ዉስጥ መሆን ያለበት ይሄዉ ነዉ፡፡ ነገር ግን ወቅቱ እንደዛ አይደለም፡፡ ስለዚህም እያንዳንዱ እንቅስቃሴ ቁጥጥር መደረግ አለበት፡፡

⚡️በዋና ዋና መንገዶች ኬላ ተጥሎ እዛ አካባቢ የጸጥታ ሃይል ተሰማርቶ ከእነዚህ ዋና ዋና መንገዶች እና በቅርብ እርቀት የሚገኙ መግቢያ መዉጫወችን መቆጣጠር አስፈላጊ ነዉ፡፡ ዙሪያዉን አጥሮ ዉስጥ ያለዉን bad elements ማጥራት ተገቢነት አለዉ፡፡ በትቂቱ እንኳን እነዚህ ቦታወች አካባቢ ቁጥጥር ሊደረግባቸዉ ይገባል፡፡በጊዚያዊነት ይህ አስፈላጊ ነዉ፡፡ ቢያንስ ለማተራመስ በየቀዳዳዉ የሚገባዉን ቁሳቁስ ማስቀረት ይቻላል፡፡

መተማ-ቋራ እና መተማ-አብደራፊ

አብደራፊ-ሁመራ እና ዳንሻ-ሳንጃ መስመር

ቡሬ-ወለጋ መስመር

ዋግምራ-ኮረም

ቋራ-ደልጊ መስመር

በለሳ (ጉኃላ)-ከትግራይ ጋር የሚዋሰንበት መስመር

ቆቦ-መስመር

ከሚሴ፤

ደጀን

ደብረብርሃን

አዋሽ-መስመር

ባቲ -ከሚሴ

ባቲ ሚሌ መስመር

ሚሌ-ጭፍራ-ወልደያ መስመር

ፓዊ-ባህርዳር መስመር

ቻግኒ-ግልገል በለስ መስመር

ሽሬ-አድርቃይ

ጠለምት/በሰሜን ፓርክ በኩል

አልፎ አልፎ መሃል መስመሮች ላይ ድንገተኛ ፍተሻ እና ቅኝት ያስፈልጋል፡፡ ለምሳሌ ከ ወልደያ-ደብረብርሃን-አዲስ፤ ከጎንደር ባህርዳር፤ ከባህርዳር ደብረ ማርቆስ፤ ከወልደያ-ሰመራ፤ ከደብረታቦር-ወልደያ፤ ከመተማ ጎንደር- ከላሊበላ-ሰቆጣ እና የመሳሰሉት፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*

x

Check Also

ብዙ ጊዜ እውነትን ውሸት ይቀድመዋል-የሺሃሳብ አበራ

ብዙ ጊዜ እውነትን ውሸት ይቀድመዋል፡፡ እውነት ዳተኛ ናት ወይም ቶሎ አትገለፅም፡፡ እውነት ቶሎ መገለፅ ባለመቻሏ ምክንያት በዓለም ...