ክቡር አቶ አሊ እንድሪስ የአስጨናቂው ዘመን የህዝብ ልጅ – በለጠ ሞላ

ክቡር አቶ አሊ እንድሪስ፤ የመዐሕድ ምክትል ሊቀመንበር የነበሩ፤ በአስጨናቂ ግዜ የህዝብ ልጅ ሆነው የተከሰቱ፤ ከፕ/ር አስራት ወልደየስ ጋርም ሆነው ሲወድቁና ሲነሱ፣ ሲታሰሩና ሲፈቱ፣ ለህዝባቸውና ለሀገራቸውም የነፃነት ውጋገን ሲሉ ብዙ መከራን የተቀበሉ ታላቅ አባት!
ትላንት ሲፈልጉት ያጡት ህዝብ ዛሬ ተገለጠና ትውልዱ ሁሉ እንዲህ ይዘክራቸዋል!
በርግጥስ ዛሬም ቢሆን ቀዳሚው ድላችን አማራውን አማራ ማድረግ መቻል አይደለምን!?
————-
ሙስሊሙ ህዝባችን አብንን እንደስጋት እንዲያየው ሰፊ አሉቧልታና አፍራሽ ቅስቀሳ ሲደረግብን ኖሯል። እኔ ደግሞ ይህን እላለሁ፦ አብን ግን አማራ ብቻ ነው! አለቀ!!

በአብን ውስጥ ፀረ እስልምና አጀንዳ ሊኖር ይቅርና ለማንኛውም የሠው ልጅ እምነት ጥሩ ያልሆነ አተያይ ያለው አንድስ እንኳ አባል በኛ መሀል ቢገኝ እሱ ከእኛ ወገን እንደማይሆነው ሁሉ እኛም ከእሱ ወገን አይደለንም! ይህም አማራዊ ቃላችንና ግብራችን ነው!
—————
ሙስሊሙ ህዝባችን እንዳይደራጅና አጀንዳውን ወደፊት እንዳያመጣ ሲሰራበት የቆየውን ደባ ፈፅሞ የምንዘነጋው አይሆንም። እስከምናውቀውም ድረስ አብን ሙስሊሙን አማራ አያቅፍም ብለው የአሉቧልታን ፍሬ ከሚዘሩት ውስጥ ግንባር ቀደሞቹ ራሳቸው የእስልምና እምነት ተከታይ ያልሆኑ፣ መረጃወቻቻን እንደሚጠቁሙትም አንድ ወቅት የፀረ እስልምና አስተሳሰብ አራማጆች የነበሩ፣ ብዙ ግዜ እንደምናያቸውም የአሉቧልታና ተራ ስም ማጥፋት ልክፍት ያለባቸው፣ ከእስልምናም ይሁን ከክርስትና ወይንም ከማንኛውም ሀይማኖታዊ አስተምህሮትና እሴቶች እልፍ ክንድ የራቁ ግለሰቦች (እንዲሁም ቡድኖች) ናቸው።
————–
ይህ ብቻም አይደለም! አብንን በሙስሊሙ ህዝባችን ዘንድ ሰፊ ቅቡልነት እንዳይኖረው የሚተጉት እነሱ በፖለቲካ መስመራቸው ከአብን ብሎም ከአማራ ህዝብ አንፃር በተቃርኖ ትርክት የቆሙ እንደሆኑም እናውቃለን።
እንደኔ ምኞትና ቁጭት ቢሆንማ እንዴውም ሙስሊሙን ህዝባችንንና የፖለቲካ ተሳትፎውን ሳስብ እጅግ ደባ የተፈፀመበት እንደሆነ እረዳለሁና ይህንን አስመልክቶ ለበርካታ ሙስሊም አማራ ወገኖቸ ቁጭቴን ደጋግሜ ገልጫለሁ ልናደርግ የሚገባውንም ስራ እንዲሁ ስንመክር ቆይተናል።
አንድ ሀቅ ግን አለ! በአብን ውስጥ ተኪ የሌለው አማራዊ ሚናን ከሚጫወቱ ወንድምና እህቶች መካከል በነብዩ ሞሀመድ አስተምህሮት ተቀርፀው ያአመሩ የአማራ የቁርጥ ቀን ልጆች እልፍ ናቸው!

አዎ!
ሙስሊሙ ህዝባችን በንግድ ስራና የልማት መስመር የሚደነቅ የተሳካ ስምሪት እንዳለው ሁሉ፤ ምኞታችን ግን ብዙ አቅም ያላቸው ወንድሞችና እህቶች በንግድ ስራ ብቻ እንዳይወሰኑና ሱቅ ጠባቂ ሆነው ከፖለቲካው እንዳይርቁ ጭምር ነው! ይልቁንም እንዲህ እንዲሆኑ የሚፈልገው አጠቃላይ የሙስሊሙ ወገናችን ፖለቲካዊ ተሳትፎና ወሳኝነት እንዳይረጋገጥ የሚወድ አማራ-ጠሉ ሀይል ብቻ ነው (ይህንንም እስኪበቃን አይተነዋል፣ እናውቃቸዋለንም)።
እናም የህዝባችን ልጆች ለአሉቧልታ እጅ ሳይሰጡ በአማራዊው የፖለቲካ መስመር ውስጥ ግንባር ቀደም ተሳታፊ በመሆን የፖለቲካ አጀንዳወችን እየቀረፁ እንዲታገሉና እንዲያታግሉ ለጥያቆወቻችንም መልስ ማግኘት ከዚህም በላይ በወሳኝነት እንዲጥሩ ነው!
————————-
ለማስታወስ ያህል! ወሎ የንስሮቹ የእነ የሱፍ ኢብራሂም፣ ሶፍያ ኑሩ፣ አዚዛ እድሪስ፣ ዘሪሁን ገሠሠ፣ መሀመድ ሻታ፣ ሞሀመድ አህመድ፣ Ras Hamelmal…..የእልፍ አእላፎች ቀየ ናት! እንግዲህ ከእነሱ በላይ የወሎ አማራ ካለ፣ ከእነሱም በላይ ሙስሊም ነኝ የሚልና ለእስልምና እቆረቆራለሁ የሚል ካለ እኛ አናውቅም!
ይሄው ነው!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*

x

Check Also

ብዙ ጊዜ እውነትን ውሸት ይቀድመዋል-የሺሃሳብ አበራ

ብዙ ጊዜ እውነትን ውሸት ይቀድመዋል፡፡ እውነት ዳተኛ ናት ወይም ቶሎ አትገለፅም፡፡ እውነት ቶሎ መገለፅ ባለመቻሏ ምክንያት በዓለም ...