አዴፓ የለውጡ ለኳሽ እና ጉልበት – ሚኪ አማራ

በመጀመሪያ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እንኳን ለአንደኛዉ አመት በአል አደረሰዉ እላለዉ፡፡ በመቀጠል የአቶ ገዱ የመቀሌ እና ጎንደር ጎሃ ሆቴል ከህወሃት ጋር ያደረገዉ ትንቅንቅ፤ የዶ/ር አምባቸዉ እና የጌታቸዉ አሰፋ የአንገት ላንገት መተናነቅ፤ የደመቀ መኮነን የኮሎኔል ቤት በከባድ መሳሪያ አይመታም ማለት፤ የገዱ ኮሎኔሉን ከጎንደር ወደፌደራል አይሄድም ማለት፤ የለማ እና የዶ/ር አብይ እንዲሁም በዛን ወቅት የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ሃላፊ (ስሙን ረሳሁት) ለማሰር ከፍርድ ቤት የመጣ የእስር ትዛዝ (አባዱላ ተስማምቶበት) ይሄን ወረቀት ከፈለክ ጠቅልለህ ሽንት ቤት ተጠቀምበት እነዚህን ሰወች መንካት አትችልም ያለዉ አቶ ገዱ፤ ዶ/ር አብይ ደህንነቱ አደጋ ላይ ሲወድቅ ና እኔ ጋር ማንም አይነካህም ያለዉ ደመቀ፤ የህወሃትን የሚዲያ ፕሮፖጋንዳ የታገለዉ ንጉሱ፤ የህወሃትን የኢኮኖሚ የበላይነት በፈርጅ በፈርጁ በማቅረብ የሙስና ሰንሰለታቸዉን ነቅሶ በማዉጣት የሞገተዉ ሟቹ ተስፋየ፤ የህወሃት የበላይነት የለም ከምትሉኝ ሰይጣን መላእክ ይሆናል ብትሉኝ ይቀለኛል ያለዉ ሻምበል በኋላም በደህንነት ታስሮ በደመቀ አፈላላጊነት የተገኘዉ እና መሰል የብአዴን ሰወች ነበሩ ህወሃትን ወደ ሽባነት የቀየሩት፡፡ ይሄ ብቻ አይደለም ብአዴኖች ህወሃትን ብቻ አይደለም የተዋጉት ከ 80 በመቶ በላይ የሚሆነዉ ኦህዴድ እራሱ የህወሃት ደጋፊ ነበር እነ አባዱላን፤ እነ ግርማ ብሩን እራሱ ወርቅነህ ገበየሁን፤ ኩማ ደመቅሳን፤ እነ አስቴርን እና መሰል ኦህዴዶችን ሁሉ ብአዴን መጋፈጥ ነበረበት ለዉጡ እንዲመጣ፡፡ እሱ ብቻ አይደለም 98 በመቶዉ የደህዴንን ሰወች መጋፈጥ ነበረባቸዉ ጠቅላይ ሚኒስተር ሃይለማሪያምን ጨምሮ እነ ሽፈራዉ ሽጉጤን፤ ደሴ ዳልኬን፤ እና የመሳሰሉትን፡፡ እሱ ብቻ አይደለም ብአዴን እራሱ ዉስጥ የነበረዉን የሀገሪቱን አድራጊ ፈጣሪ በረከትን መታገል ነበረበት፡፡ እናሳ አሁን ለዉጡ ሲባል ከትንሽ እስከ ትልቅ ቲም ለማ ለሚባል ቡድን ሁሉንም ነገር አስታቅፎታል፡፡ እነሱም የሰሜን ሰዉን ይሉኝታነት ስለሚያዉቁት ዝም ብለዉ ወሬዉን እንደ እዉነት ይቀበሉታል፡፡ well, ይሄን ብአዴን ከፈለገ claim ማድረግ ይችላል ካልፈለገ አያገባኝም፡፡

የእኔን፤ የጓደኞቼን እና የአማራ ወጣትን ተጋድሎ ግን ማናባቱም ዘርፎ መዉሰድ አይችልም አሳልፌም አልሰጥም፡፡ አክስቴ እንደምትለዉ ከቅርብ የተገኘ ጸበል የልጥ መንከሪያ ይሆናል እንደተባለዉ ነዉ እንጅ ቁጭ ብለን ብንተሳሰብ በጣት ከሚቆጠሩት የኦህዴድ ሰወች በቀር የሚኪን ያክል አስተዋጽኦ አላረጉም እንኳን አይደለም የአማራን ወጣት ትግል ያህል ሊያደርጉ፡፡ አረ እንዲያዉ ክላ ወዲያ፡፡ የአማራን ወጣት ባናደራጀዉ እና ባናቀሳቅሰዉ ይሄኔ እኔ ነኝ የለወጥኩት የሚለዉ ሃይል ሁሉ ቢጫ የእስር ልብሱን ለብሶ ሰኞ ሰኞ አሸባሪወች የልደታ ምድብ ችሎት ቀርበዉ የ 14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ተጠየቀባቸዉ እያለ እየተመላሰ ነበር፡፡እዛዉ ከፈለክ የብአዴንን ተጋድሎ ዝረፍ እንጅ የአኔን፤
የጓደኞቼንና የአማራን ህዝብ ትግል ማንም አይሰርቅም አይክድምም፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*

x

Check Also

ብዙ ጊዜ እውነትን ውሸት ይቀድመዋል-የሺሃሳብ አበራ

ብዙ ጊዜ እውነትን ውሸት ይቀድመዋል፡፡ እውነት ዳተኛ ናት ወይም ቶሎ አትገለፅም፡፡ እውነት ቶሎ መገለፅ ባለመቻሏ ምክንያት በዓለም ...