የአማራ ብሄርተኝነት ለአማራ ህዝብ -ልጆቹን እና ማንነቱን ነጥቀዉት የሚሮጡ ወሮ በሎችን የማስጣያ እና ማስመለሻ መሳሪያዉ ነዉ

[the_ad_placement id=”middle”]◆የአማራ ብሄርተኝነት የአማራን ህዝብ ወዳጅና ጠላቱን በቅጡ ለይቶ የሚረዳበት መነፅሩ ነዉ! ——————- ሰሞኑን ህዝባችንን በማደራጀት ስራዎች ላይ ተሰማርተን ነበር። በርግጥ ይሄንኑ አጠናክረን እንቀጥላለን። የአማራ ግዛት የጠፍ መሬት(ማንም ሊመራዉ የሚችል -Res Nullis) የሚመስላቸዉ ሰዎች ይህ አለመሆኑን ህዝቡ በቅጡ እያስገነዘባቸዉ ይገኛል! —- የአማራ ህዝብ የማንነት ትግል ረጅም ርቀትን ተጉዟል፣ በርካታ ድንበሮችንም ተሻግሯል፣ አሜኬላዎችን እያነሳና እየተራመደ “አማራ የለም” ሲሉ የነበሩትን ጭምር ከፊት ለፊታቸዉ ደርሶ እንኳን አማራ እናንተም አላችሁ ሲላቸዉ አሁን እነሱ የት እንዳሉ በማይታወቅበት ሁኔታ ላይ ይገኛሉ። —– የአማራ ህዝብ እልህ አስጨራሽ ዉጫዊና ዉስጣዊ ትግሎችን አካሂዷል። እንኳን ያስፈራራዉን ይቅርና ጦር የሰበቀዉን ሁሉ አንገት አስደፍቷል። ቀጣይ አይቀሬ የሆኑት የአማራ ህዝብ አጀንዳዎችና ጥያቄዎች በርካታ ጉጅሌዎችን ብርክ አስይዞ እያስባተታቸዉ ይገኛል። አሁን በአማራ ጠል ሰዎች የዛቻ ድምፅ ዉስጥ የሲቃ ቅላፄ መስማት የተለመደ ነዉ!!! ——– የአማራ ብሄርተኝነት የአማራ ህዝብ የትግል ዉጤት ሲሆን የማንነትና የህልዉና ትግሉ መነሻም ነዉ። ህዝባችን እየታገለ ያለዉ በአንድ በኩል በአፈሙዝ የታገዘዉን ጨቋኝ ስርአት ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ከተለያዩ አቅጣጫዎች በገሀድና በህቡዕ የተከፈቱበትን የፕሮፖጋንዳ ዘመቻዎች ነዉ። ምስጋና ለአማራ አርበኛ ልጆች ይገባቸዉና በሁሉም ዘርፎች የተከፈቱትን ጥቃቶች እያከሸፏቸዉ ነዉ!!! ነገር ግን የተያዘዉ ጉዳይ የአማራ ህዝብ ስለሆነ አሁንም ይሁን ወደፊት ጠላቶቹ በርካታና ተኝተዉ የማያድሩ መሆናቸዉ ሊታወቅ ይገባል። —– በአሁኑ ጊዜ የአማራ ህዝብ ትግል የህልዉና ጥያቄዎቹን ቢያንስ ማስመለሱ እንደማይቀር ግንዛቤ ሲወሰድ የማርከሻ እሳቤዎችን ቀምረናል የሚሉ ወገኖች ከዚህም ከዛም ብቅ እያሉ ይገኛሉ። በዚህ ረገድ በአብዛኛዉ ሰሞኑን የታደምናቸዉን ባጠቃላይ እንደሚከተለዉ ማየት እንችላለን። አንዱ ዘርፍ ለናት ምጥ የማስተማር አይነቱ “ዜግነት እና ኢትዬጵያዊነት ብቻ” የሚለዉ ሆኖ እናገኘዋለን። —— “ኢትዬጵያዊነት ብቻ” የሚለዉ ሀሳብ በአብዛኛዉ የሀገራችን ክፍሎች ላይ ተዘርቶ የጋሸበ ስለሆነ አዋጭ አይደለም። በተለይ የኢትዬጵያዊነት ምድረበዳ መላ ሀገሪቱን አጥለቅልቋት በነበረበት ወቅት ብቸኛዉ የኢትዬጵያዊነት የዘር ባንክ ሆኘ አገለግላለሁ ያለዉ የአማራ ህዝብ በዚህ ምክንያት የከፈለዉን ከባድ ዋጋ ራሱ ያዉቀዋል። — ◆እንግድህ ዛሬ ሌላ ቀን ነዉ! የአማራ ህዝብ በዚህ በረሃማነት ከመጥፋት ለመዳን ይሄን በብቃት መቋቋም የሚችል “የአማራ ብሄርተኝነት” የሚባል ዛፍ ለመትከል ተገዷል! የአማራ ህዝብ ይሄን ያደረገዉ በሰይጣንና በጥልቅ ባህር አጣብቂኝ መካከል ከወደቀ በኋላ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል። — ስለሆነም የአማራ ብሄርተኝነት ምርጫ ከምርጫዎች ሁሉ በኋላ ተመዝኖ የተያዘ በመሆኑ እንደዋዛ የሚለቀዉ ጭብጦ አይሆንም ማለት ነዉ። —– ከአማራ ብሄርተኝነት በተፃራሪ የሚሰለፉ ወገኖች የተለያዩ ቢመስሉም በአማራ ህዝብ ጥላቻቸዉ ወይንም በመዳረሻቸዉ ይመሳሰላሉ። በነገራችን ላይ ሌሎች ብሄርተኛ ድርጂቶችም በግልፅ አማራ ጠል አቋማቸዉ ይስማማሉ። — በደፈናዉ ሲታይ ይህ የሀሳብ መዳረሻ ጥሩ ይመስላል። ይህ የአማራ ህዝብ የዘመናት አቋም የነበረ መሆኑን ግን በእጅጉ ይዘነጉታል። በርግጥ አማራ ይሄን የ”ኢትዬጵያ ብቻ” ሀሳብ ማራመዱ ጥላቻንና ሰቆቃን ከመጋፈጥ ዉጭ ያተረፈዉ አንዳችም ነገር የለም። —- “ኢትዬጵያ ብቻ” የሚለዉን እሳቤ የአማራ ህዝብ በተግባር አራምዶትና በዚህም ምክንያት ዘግናኝ መስዋእትነትን ከፍሎ የፈተሸዉን እሳቤ አሁን ከቃልና ከፅሁፍ ያላለፈዉን እንደገና የሚሸምትበት አመክንዬ ከየት ይመጣል?! —— አንዳንድ ልሂቃን ሰሞኑን የግል መብት ወይንስ የቡድን መብት ይቅደም? የሚለዉን ጥያቄ እዚህ ሀገር የጀመረ ጉዳይ አስመስለዉ ደረቅ ምርጫ አድርገዉ ሲያቀርቡልን እየታዘብን ነዉ። ይህ በፍልስፍና ትምህርት ረገድ እድሜ ጠገብ ሆኖ ነገር ግን ያልተፈታ ጉዳይ መሆኑን አናዉቅ ይሆን? — አቀንቃኞቹ በተሳሳተ መልኩ (ሆነ ብለዉ የሚሉትን ይጨምራል) በተለይ ታሪካዊና ነባራዊ ተጨባጮች እንደሌሉ አድርገዉና ደልዘዉ እያሰሙንና እያስነበቡን ይገኛሉ። ይሄን ሀሳብ ማመን ወይንም መቀበል አንድ ነገር ሆኖ በፍሬ ነገሮች ክህደት ላይ የተመሰረተ ሲሆን ግን አይመችም። (Everyone is entitled to his opinions but not to facts!!!) —- 1/ በአሁኑ ጊዜ የግለሰብም ይሁን የቡድን መብት በአለምአቀፍ ህግጋትና ድንጋጌዎች ጭምር እዉቅና የተሰጣቸዉ መብቶች ናቸዉ። ሰሞኑን ይሄን ጉዳይ የሀሰት ምርጫ አድርገዉ በየመድረኩና በየሚዲያዉ ሲያስተጋቡት እየተመለከትን ነዉ። ኢህአደግም ሲጨንቀዉ አንድ ሀገራዊ ፖርቲ ልሆን ነዉ እያለ ይገኛል። አያይዞም ” ራስን በራስ የማስተዳደር መብት እንደተጠበቀ ይቆያል” በሚል ገልፇል። ይህ ምን ማለት ነዉ? የዚህን ዉጤት አብረን የምናየዉ ይሆናል። —- 2/ አንድ ቡድን የግለሰቦች የቁጥር ድምር ብቻ አድርጎ የሚወስድ እሳቤ የተሳሳተ ነዉ። —— 3/ የአማራ ብሄርተኝነትን ለመደገፍና ለማራመድ ብሶት አንዱ ምክንያት መሆኑ ይታወቃል። ነገር ግን የአማራ ብሄርተኝነት በብሶት አምድ ብቻ ተደግፎ የቆመ አይደለም። —— አሁን የአማራ ብሄርተኝነት ቋሚ መርህ ነዉ። የአማራ ብሄርተኝነት የአማራ ህዝብ ብቸኛ የመወከያና የመደራደሪያ እሴት ነዉ። ◆የአማራ ብሄርተኝነት የአሁንና የቅርብ ሳይሆን ወደፊት ላሉት ዘመናት ሁሉ የሚያገለግል የፍትህና የእኩልነት መሳሪያ ነዉ። ለአማራ ህዝብ ብሄርተኝነቱ እጣፋንታዉን በራሱ እዝ ስር የሚያዉልበት ስንቅና ትጥቁ ሲሆን ህልዉናዉ በግምት ላይ የተመሰረተና በሌሎች ወገኖች ይሁንታ ላይ የተንጠለጠለ እንዳይሆን የሚያደርገዉ ነዉ። — የአማራ ብሄርተኝነት የአማራን ህዝብ ወዳጅና ጠላት በቅጡ ለይቶ የሚረዳበት መነፅሩ ነዉ። የአማራ ብሄርተኝነት የአማራን ህዝብ ጠላቶችና የህልዉና አደጋዎችን የሚመክትበት በትሩ ሲሆን መብቶቹን፣ ይዞታዎቹን እና ልጆቹን ነጥቀዉት የሚሮጡትን ወሮ በሎች ማስጣያ እና ማስመለሻ ጦርና ጎራደዉም ነዉ! ◆አንድነት ማለት አማራነትን መደምሰስ አድርገዉ የሚወስዱትን መለየት የቻልነዉ ከምር አማራ መሆን በመቻላችን ነዉ። የዚህ ዘመን የአንድነት እሳቤ የአማራ ልጆችን የማታለያና የማባከኛ ስልት ስለመሆኑ ቀድመን እና ደጋግመን የተናገርነዉ በየሂደቱ እየተረጋገጠ መጥቷል። የፀረ አማራ ትርክት ያነገቡ ሰዎች ለዘዉጌ ፖለቲካ እሳቤያቸዉ የቀጥታ ማስፈፀሚያ ማእቀፍ ሲያጥራቸዉ በአንድነት ጎራ ለያዉም ፊት አዉራሪ ሆነዉ ብቅ የሚሉበት ሁኔታ የተለመደ ነዉ። ◆በቅርቡ ደግሞ በተለይ ይህ አካሄድ በአማራ መደራጀት ምክንያት ሀቁ እየታወቀና እርቃኑን እየቀረ ሲመጣ “ተመልሸ ወደ ጡዜ” እያሉ የሚገኙ ሲሆን በዚህ አግባብ ወደ-ጉህን- በሀቅ ለመመለስ የራቀበት ደግሞ በፀረ አማራ አማካኝ መስመር ላይ ለመንጋለል በቅቷል። ማየትና መገንዘብ ለሚችል ሰዉ (one who can reflect) እያንዳንዷ ሀገራዊ የፖለቲካ ጠብታ አማራ ለሆነ ሁሉ የብሄርተኝነት ችግኙን ለማልማት የመስኖ ግብአት ሊያዉለዉ የሚገባ ነዉ! የአማራ ብሄርተኝነት የአማራ ህዝብ ሁለመናዉና ህልዉናዉ ነዉ!!! ——- “የአማራ ብሄርተኝነትን “አማራ ጠል ድርጂቶች ይፈልጉታል” የሚል ድስኩር ስንሰማ መገረማችን አይቀርም። ይህ ሀሳብ መፃፍና መናገር እችላለሁ ለማለት ያክል የተሰነዘረ ብቻ ነዉ። ይህ አንድን ነገር የሚጠላ ሌላዉን ይወዳል የሚል ያላፊ አግዳሚ አመክንዬም ነዉ። እነዚህ ሰዎች የአማራን ህዝብ የኢትዬጵያዊነት እሳቤ የሚጠሉ ቡድኖች አማራነትን ግን ይወዳሉ ነዉ እያሉን ያሉት። — አማራ ከህፃን እስከአዋቂ ያለዉን አማራ ሁሉ የሚያፈናቅሉና የሚዘርፉት ለምን ይሆን? ለሚለዉ ጥያቄ መልስ አይሰጥም። —— እዉነታዉ በማንኛዉም እድሜ፣ ፆታ፣ ሀይማኖት፣ ሰፈር፣የኑሮ ሁኔታ፣ የፖለቲካ እሳቤ ላይ ያለዉን አማራ ማጥቃት የአማራ ጠሉ ጉጅሌ ሁሉ አላማና ትግበራ ስለመሆኑ ይካድ ይሆን? —— በመጨረሻ ግን አንድ እዉነታ በተለየ መልኩ ገዝፎ መጥቷል እሱም አማራ እና የአማራ የሆነዉ ሁሉ ማንም ተነስቶና እንደፈለገ የሚመራዉ የጠፍ መሬት(Res Nullis) አለመሆኑ እየተረጋገጠ መጥቷል! ◆የአማራ ብሄርተኝነት “አማራ የጠፍ መሬት ነዉ” የሚለዉን በገሀድም ይሁን በድብቅ የተያዘ እሳቤ ቀድሞ በመረዳት እና በመለየት የሚከላከልበት Militant Democracy ዘይዶ ተፈፃሚ እንደሚያደርግ ይጠበቃል። ራሱን የማይከላከል ዴሞክራሲ እንደትስ ይኖራል? ————- አመሰግናለሁ!!!

5 comments

 1. በርቱ ጠንክራች ሥሩ፤ ዓለም ሁልጊዜም የአሸናፊዎች ነች፤ አስተዋይነት፣ ብልህነት፣ የውስጥ አንድነት፣ አርቆ አሳቢነት እና ቀድሞ መገኘት መለያችሁ ሊሆን ይገባል፡፡

 2. The body can through two paragraphs to a website in span.
  Choose a column on the far right where banner or text ads can air in between them.
  However, people who could develop good content s are quite limited. https://918kiss.poker/casino-games/72-playboy-casino

 3. This is a topic whicһ iss close to my heart… Many thanks!
  Ԝhere arе your congact details though? https://itsmyurls.com/outbound/5bdc4d227f92a4de0bcba872

 4. You have safe browsing, crash control, application shortcuts.
  and simpler downloads to mention a few more. He became a “rock star”, during the Arias trial, much on the dismay on the defense an opinion. http://publicradioboston.org/__media__/js/netsoltrademark.php?d=win88.today%2Fdownload-mega888-android-ios%2F

 5. It is tduly a great and uѕeful piece of info. I am glad that you simply shared this hepful іnformation with us.

  Please keep us nformed like this. Thank you for ѕharing. http://aggieanimaldentalservice.com

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*

x

Check Also

ብዙ ጊዜ እውነትን ውሸት ይቀድመዋል-የሺሃሳብ አበራ

ብዙ ጊዜ እውነትን ውሸት ይቀድመዋል፡፡ እውነት ዳተኛ ናት ወይም ቶሎ አትገለፅም፡፡ እውነት ቶሎ መገለፅ ባለመቻሏ ምክንያት በዓለም ...