የአለምን ኢኮኖሚ ማን ይመራዋል?-ሚኪ አማራ

የአለምን ኢኮኖሚ ማን ይመራዋል በደረጃ ብለህ ሀገሮችን ስትዘረዝር እንዲህ እያለ ይሄዳል 1) አሜሪካ 2) ቻይና 4) ጃፓን 3) ጀርመን 5) ፈረንሳይ ብለህ ስድሰተኛ ላይ እንግሊዝን በመቅደም አንድ የአሜሪካ ስቴት ካሊፎርኒያ ይመጣል፡፡ እናም የእኔ ፍላጎት 50 ሚሊየን የአማራ ህዝብ ጠንካራ የኢኮኖሚ ባለቤት ማድረግ ነዉ፡፡ የሰዉ ሃይል አለ፤ ሪሶርስ አለ፤ እንደ አባይ አይነት በተፈጥሮ የተቸረን ሃብት አለ፡፡ ምቹ የአየር ሁኔታ እና ለግብርና ተስማሚ የሆነ ሰፊ መሬት አለ፡፡ በአርግጥ አጠቃላይ ኢትዮጵያዉን ሃብት አፍርተዉ ጥሩ ኑሮ እንዲኖሩ ፍላጎቴ ነዉ (ፖለቲከኞችን አይጨምርም).

የመጀመሪያዉ የሚያስፈልገን ለኢኮኖሚ አድገት ዋና ግብአታችን ምንድን ነዉ የሚለዉ ነዉ፡፡ Cobb-Douglas production function እንደሚለዉ የአንድ ሀገር የኢኮኖሚ እድገት የሶስት ነገሮች ዉጤት ነዉ፡፡ ይሄም Innovation, labor, and Capital ናቸዉ፡፡ እነዚህን ሶስት ሃብቶች አጣምሮ የያዘ ሀገር በጣት የሚቆጠሩ ናቸዉ፡፡ ነገር ግን ሃገራት እራሳቸዉን ገምግመዉ ያላቸዉን ሃብት ባግባቡ ተጠቅመዉ ህዝባቸዉን ከድህነት ያወጣሉ፡፡ የአሜሪካ ኢኮኖሚ የሶስቱ ድምር ዉጤት ነዉ፡፡ ካናዳ innovation እና labor እጥረቱ ስላለ capital (ማሽነሪዎች እና የመሳሰሉት) ታተኩራለች፡፡ ቻይና የኢኮኖሚ እድገቷን ያስመዘገዘገችዉ የሰዉ ሃይሏ (labor) ላይ በማተኮር በከፍተኛ ሁኔታ የግብርና እና ኢንደስትሪ ምርትን በማሳደግ ነዉ፡፡

ኢትዮጵያም ወይም አማራ ኢኮኖሚዉን ማሻሻል ከፈለገ እየባከነ ያለዉን የሰዉ ሃይል ወደ ስራ በማስገባት የምርት መጠን ማሳደግ ይቻላል፡፡ በነገራችን ላይ አሁን ላይ በልሂቃን ዉስጥ የሚደረገዉ ቁርቁስ ባብዛኛዉ ፖለቲካዊ ሚመስለዉ ነገር ጎልቶ ይዉጣ እንጅ ወደ ዉስጥ ገባ ብለን ካየነዉ ኢኮኖሚያዊ ነዉ፡፡ ኢኮኖሚክስን ከላይ እሰከታች ብታገላብጡት ከሁለት ነገሮች ሌላ ምንም አታገኙም፡፡ የንብረት መብት (property right) እና competitive market (ነጻ ወይም የዉድድር ገቢያ)፡፡ ስለዚህም አዲስ አበባ የኔ ነዉ ስትል የንብረት መብት (property right) ነዉ እየጠየቅ ያለኸዉ፡፡ property right ደግሞ የመደራደር አቅም (bargaining power) ይሰጥሃል፤ ህብት የማፍራት እና የማሳደግ መብት ይሰጥሃል፤ የመሸጥ እና የመለወጥ መብት ይስጥሃል፡፡ ለምሳሌ የቤንሻንጉል ክልል ባለቤትነቱ የጉሙዝ እና ሽናሻ ነዉ ሲባል ምን ማለት ነዉ property right (የንብረት መብትነቱ) የተሰጠዉ ለእነዚህ ሰወች ነዉ ማለት ነዉ፡፡ ሌላዉ በተፈለገ ጊዜ ይባረራል ማለት ነዉ፡፡ ምክንያቱም ይህ ኢኮኖሚክ right አልተሰጠዉም፡፡ ኢትዮጵያ ዉስጥ ያለዉ ፍትጊያ መጨረሻዉ economic justice ወደ ማስፈን ያዘነበለ ነዉ ማለት ነዉ፡ ሁሉም ሰዉ በኢትዮጵያ ላይ ወይም በማንኛዉም ክልል ላይ property right እንዲኖረዉ ማድረግ ማለት ነዉ፡፡

ለማንኛዉም ተረባርበን አሉ የሚባሉ የ economic policy instruments ተጠቅመን ለራሱ ብቻ ሳይሆን ለምስራቅ አፍሪካ እና መካከለኛዉ ምስራቅ የሚተርፍ ምርት አምራች እና በኑሮዉ የበለጸገ ህዝብ እንዲኖረን እናደርጋለን፡፡ እናደርገዋለን ስልህ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*

x

Check Also

ብዙ ጊዜ እውነትን ውሸት ይቀድመዋል-የሺሃሳብ አበራ

ብዙ ጊዜ እውነትን ውሸት ይቀድመዋል፡፡ እውነት ዳተኛ ናት ወይም ቶሎ አትገለፅም፡፡ እውነት ቶሎ መገለፅ ባለመቻሏ ምክንያት በዓለም ...