አሁን ያለው ህገ መንግስት ከመጽደቁ በፊት የኢትዮጵያ ህዝብ ከተሰጠባቸው ውስጥ ዘጠኙ ውሳኔዎች | ውብሸት ሙላት

  • አሃዳዊ መንግሥትን የመረጡ- ሶማሌ 54 በመቶ

የአሁኑ ሕገ መንግሥት ከመጽደቁ በፊት በየክልሎቹ በተደረጉ ዉይይቶች መሠረት የተወሰኑ ጉዳዮች ላይ የድጋፍ እና ተቃዉሞ ድምጽ ተሰብስቧል፡፡ ድጋፍ ከተሰጠባቸዉ ነጥቦች ዉስጥ አንዱ የመንግሥት አወቃቀር ሥርዓቱ አሃዳዊ ይሁን ወይስ አይሁን የሚለዉ ይገኝበታል፡፡ የድጋፍ ዉጤቱ እንደሚከተለዉ ነበር፡፡

ክልል 1 (ትግራይ)- 1 %

ክልል 2 (አፋር) -3 %

ክልል 3 (አማራ) – 8 %

ክልል 4 (ኦሮሚያ) -2 %

ክልል 5 (ሶማሌ)- 54 %

ክልል 6 (ቤኒሻንጉል/ጉሙዝ)-14 %

ክልል 12 (ጋምቤላ) -23 %

ክልል 13 (ሐረሪ)- 3 %

ክልል 14 (አዲስ አበባ)- 8 %

ትዝብት፡- የሰማሌ እና የጋምቤላ ክልሎች ለአሃዳዊ ሥርዓት የሰጡት ድጋፍ እና ሁልጊዜ አሃዳዊ መንግሥት ናፋቂ የሚባለዉ የአማራ ክልል የሰጡ ድጋፍ በዚህ መጠን ዝቅ ማለት!

  • አማርኛ የጋራ ቋንቋ እንዲሆን ትግራይ 64፣ኦሮሚያ 91 በመቶ ……

የአሁኑ ሕገ መንግሥት ከመጽደቁ በፊት በየክልሎቹ በተደረጉ ዉይይቶች መሠረት የተወሰኑ ጉዳዮች ላይ የድጋፍ እና ተቃዉሞ ድምጽ ተሰብስቧል፡፡ ድጋፍ ከተሰጠባቸዉ ነጥቦች ዉስጥ አንዱ የጋራ መገናኛ ቋንቋው አማርኛ ይሁን ወይስ አይሁን የሚለዉ ይገኝበታል፡፡ የድጋፍ ዉጤቱ እንደሚከተለዉ ነበር፡፡

ክልል 1 (ትግራይ)- 64 %

ክልል 2 (አፋር) – 99 %

ክልል 3 (አማራ) – 98 %

ክልል 4 (ኦሮሚያ) – 91%

ክልል 5 (ሶማሌ)- 93 %

ክልል 6 (ቤኒሻንጉል/ጉሙዝ)- 96 %

ክልል 12 (ጋምቤላ) – 98 %

ክልል 14 (አዲስ አበባ)- 97 %

ትዝብት፡- የትግራይ 64 በመቶ ብቻ መሆኑ፣የአፋር ከአማራ ክልል የበለጠም መደገፉ፣ የኦሮሚያና የሶማሌ በዚህ መጠን መሆኑ!

  •  መገንጠል በሕገ መንግሥት አይግባሶማሌ 67 እና ጋምቤላ 62 በመቶ….

የአሁኑ ሕገ መንግሥት ከመጽደቁ በፊት በየክልሎቹ በተደረጉ ዉይይቶች መሠረት የተወሰኑ ጉዳዮች ላይ የድጋፍ እና ተቃዉሞ ድምጽ ተሰብስቧል፡፡ ድጋፍ ከተሰጠባቸዉ ነጥቦች ዉስጥ አንዱ የመገንጠል መብት በሕገ መንግሥቱ ይግባ ወይስ አይግባ የሚለዉ ነበር፡፡ መግባት የለበትም የሚለዉ ዉጤቱ እንደሚከተለዉ ነበር፡፡

ክልል 1 (ትግራይ)- 0 %
ክልል 2 (አፋር) – 20 %
ክልል 3 (አማራ) – 23 %
ክልል 4 (ኦሮሚያ) -10 %
ክልል 5 (ሶማሌ)- 67%
ክልል 6 (ቤኒሻንጉል/ጉሙዝ)-27 %
ክልል 12 (ጋምቤላ) -62 %
ክልል 13 (ሐረሪ)- 9 %
ክልል 14 (አዲስ አበባ)- 40%
ትዝብት፡- የሶማሌ እና የጋምቤላ የመገንጠል መብት መግባት የለበትም በማለት የድጋፍ መጠን እና የትግራይ ደግሞ ዜሮ መሆን!

  • በሕገ መንግሥት የተገደበ ንጉሣዊ ሥርዓት፡ቤኒሻንጉል 29፣ጋምቤላ 22፣አማራ 11 በመቶ

የአሁኑ ሕገ መንግሥት ከመጽደቁ በፊት በየክልሎቹ በተደረጉ ዉይይቶች መሠረት የተወሰኑ ጉዳዮች ላይ የድጋፍ እና ተቃዉሞ ድምጽ ተሰብስቧል፡፡ ድጋፍ ከተሰጠባቸዉ ነጥቦች ዉስጥ መንግሥታዊ ሥርዓቱ በሕገ መንግሥት የተገደበ ንጉሣዊ ሥርዓት ይሁን ወይስ አይሁን የሚለዉ ይገኝበታል፡፡ የድጋፍ ዉጤቱ እንደሚከተለዉ ነበር፡፡

ክልል 1 (ትግራይ)- 1 %
ክልል 2 (አፋር) – 3 %
ክልል 3 (አማራ) – 11 %
ክልል 4 (ኦሮሚያ) -6 %
ክልል 5 (ሶማሌ)- 10 %
ክልል 6 (ቤኒሻንጉል/ጉሙዝ)-29 %
ክልል 12 (ጋምቤላ) -22%
ክልል 13 (ሐረሪ)- 10 %
ክልል 14 (አዲስ አበባ)- 2%
ትዝብት፡- ንጉሣዊ ሥርዓት ናፋቂዎቹ ከአማራ ይልቅ ቤኒሻንጉል ጉሙዝና ጋምቤላ መሆናቸዉ፤ የሶማሌም ቢሆን 19 ከመቶ መሆኑ!

  • መሬት በግል ይዞታ ይሁን፡ሶማሌ 54፣ትግራይ 1 በመቶ ድጋፍ፤

የአሁኑ ሕገ መንግሥት ከመጽደቁ በፊት በየክልሎቹ በተደረጉ ዉይይቶች መሠረት የተወሰኑ ጉዳዮች ላይ የድጋፍ እና ተቃዉሞ ድምጽ ተሰብስቧል፡፡ ድጋፍ ከተሰጠባቸዉ ነጥቦች ዉስጥ መሬት በግል ይዞታ ይሁን ወይስ አይሁን የሚለዉ ይገኝበታል፡፡ ይሁን በማለት የደገፉት ዉጤት እንደሚከተለዉ ነበር፡፡

ክልል 1 (ትግራይ)- 1 %
ክልል 2 (አፋር) – 39 %
ክልል 3 (አማራ) – 10 %
ክልል 4 (ኦሮሚያ) -6 %
ክልል 5 (ሶማሌ)- 54 %
ክልል 6 (ቤኒሻንጉል/ጉሙዝ)-26 %
ክልል 12 (ጋምቤላ) 17 %
ክልል 13 (ሐረሪ)- 10 %
ክልል 14 (አዲስ አበባ)- 5 %
ትዝብት፡- የመሬት ሥሪት ለዘመናት ርስት በሆነባቸዉ በትግራይና በአማራ በዚህ መጠን ዝቅ ብሎ የወል (የጎሳ) በመሆነበት በአፋርና ሶማሌ በዚህ መጠን ከፍ ማለቱ!

  • አንድ የጋራ ቋንቋ የሚናገር በሰፈረበት ቤኒሻንጉል 50 በመቶ ብቻ ድጋፍ

የአሁኑ ሕገ መንግሥት ከመጽደቁ በፊት በየክልሎቹ በተደረጉ ዉይይቶች መሠረት የተወሰኑ ጉዳዮች ላይ የድጋፍ እና ተቃዉሞ ድምጽ ተሰብስቧል፡፡ ድጋፍ ከተሰጠባቸዉ ነጥቦች ዉስጥ የፌደራል ሥርዓቱ መዋቀር ያለበት አንድ የጋራ ቋንቋ የሚናገር ሕዝብ በሠፈረበት ይሁን ወይስ አይሁን የሚለዉ ይገኝበታል፡፡ የድጋፍ ዉጤቱ እንደሚከተለዉ ነበር፡፡

ክልል 1 (ትግራይ)- 99 %
ክልል 2 (አፋር) – 99 %
ክልል 3 (አማራ) – 85 %
ክልል 4 (ኦሮሚያ) -82 %
ክልል 5 (ሶማሌ)- 89 %
ክልል 6 (ቤኒሻንጉል/ጉሙዝ)-50 %
ክልል 12 (ጋምቤላ) -77 %
ክልል 13 (ሐረሪ)- 73%
ክልል 14 (አዲስ አበባ)- 81%

  • በባህል፣በታሪክና በሥነልቦና መተሳሰር ለፌደራል አወቃቀር ተቃዉሞ ትግራይ 98 ሶማሌ11 በመቶ

የአሁኑ ሕገ መንግሥት ከመጽደቁ በፊት በየክልሎቹ በተደረጉ ዉይይቶች መሠረት የተወሰኑ ጉዳዮች ላይ የድጋፍ እና ተቃዉሞ ድምጽ ተሰብስቧል፡፡ ድጋፍ ከተሰጠባቸዉ ነጥቦች ዉስጥ የፌደራል ሥርዓቱን ለማወቀር ህዝቦች በሰፈሩበት መሬት ላይ ያላቸዉ የባህል፣ የታሪክና የሥነልቦና ትስስር መለኪያ ይሁን ወይስ አይሁን መንግሥታዊ የሚለዉ ይገኝበታል፡፡ አይሁን ባለት የተቃወሙት ዉጤቱ እንደሚከተለዉ ነበር፡፡

ክልል 1 (ትግራይ)- 98 %
ክልል 3 (አማራ) – 63 %
ክልል 4 (ኦሮሚያ) -60%
ክልል 5 (ሶማሌ)- 11 %
ክልል 6 (ቤኒሻንጉል/ጉሙዝ)-16%
ክልል 12 (ጋምቤላ) -18%
ክልል 13 (ሐረሪ)- 22 %
ክልል 14 (አዲስ አበባ)- 70%

ትዝብት፡- ትግራይ በዚህ መጠን መቃወማቸዉ ምእራባዊ ዞባን (ጠገደ፣ጠለምት፣ወልቃይት፣ሁመራ) እና ራያን በማሰብ ይመስላል፤የሶማሌ ተቃዉሞ ዝቅተኛ መሆኑ ሶማሌ ከሚኖርበት ዉጭ አለመፈለጉን ያመለክታልም፡፡

  • በአስተዳደር ቅልጥፍና አመቺነት ፌደራላዊ አስተዳደር ለማዋቀር ድጋፍ ትግራይ 1፣ጋምቤላ 70 በመቶ….

የአሁኑ ሕገ መንግሥት ከመጽደቁ በፊት በየክልሎቹ በተደረጉ ዉይይቶች መሠረት የተወሰኑ ጉዳዮች ላይ የድጋፍ እና ተቃዉሞ ድምጽ ተሰብስቧል፡፡ ድጋፍ ከተሰጠባቸዉ ነጥቦች ዉስጥ የፌደራል ሥርዓቱን ለማዋቀር የአስተዳደር ቅልጥፍና መለኪያ ይሁን ወይስ አይሁን የሚለዉ ይገኝበታል፡፡ ይሁን ያሉት ዉጤቱ እንደሚከተለዉ ነበር፡፡

ክልል 1 (ትግራይ)- 1 %
ክልል 3 (አማራ) – 21 %
ክልል 4 (ኦሮሚያ) -12%
ክልል 5 (ሶማሌ)- 45 %
ክልል 6 (ቤኒሻንጉል/ጉሙዝ)-41%
ክልል 12 (ጋምቤላ) -70%
ክልል 13 (ሐረሪ)- 11 %
ክልል 14 (አዲስ አበባ)- 7%

ትዝብት፡- የአዲስ አበባና የትግራይ በዚህ መጠን መቃወማቸዉ የጋምቤላ፣ቤኒሻንጉልና የሶማሌ ክልሎች ድጋፍ የሚደንቅ ነዉ!

  • ሚዛናዊ የተፈጥሮ ሃብት ሥርጭትን በመከተል የፌደራል ሥርዓቱን ለማዋቀር የተቃወሙ፡ቤኒሻንጉል 17፣ትግራይ 99 በመቶ…..

የአሁኑ ሕገ መንግሥት ከመጽደቁ በፊት በየክልሎቹ በተደረጉ ዉይይቶች መሠረት የተወሰኑ ጉዳዮች ላይ የድጋፍ እና ተቃዉሞ ድምጽ ተሰብስቧል፡፡ ድጋፍ ከተሰጠባቸዉ ነጥቦች ዉስጥ የፌደራል ሥርዓቱን ለማወቀር ሚዛናዊ የተፈጥሮ ሃብት ሥርጭት መለኪያ ይሁን ወይስ አይሁን የሚለዉ ይገኝበታል፡፡ አይሁን በማለት የተቃወሙት ዉጤት እንደሚከተለዉ ነበር፡፡ ተቃዉሞ….

ክልል 1 (ትግራይ)- 99 %
ክልል 3 (አማራ) – 77 %
ክልል 4 (ኦሮሚያ) -90 %
ክልል 5 (ሶማሌ)- 86 %
ክልል 6 (ቤኒሻንጉል/ጉሙዝ)-56%
ክልል 12 (ጋምቤላ) -17 %
ክልል 13 (ሐረሪ)- 79 %
ክልል 14 (አዲስ አበባ)- 91%

ትዝብት፡- የጋምቤላ የተፈጥሮ ሃብትን መሥፈረት ማድረግን መምረጡ (ሃብት ቢኖራቸዉም ፍትሐዊነትን ማስቀደማቸዉ)፣ የትግራይ 99 በመቶ መቃወም ትኩረታቸዉ ሌላ የትግራይ አንድነት እንጂ በሃብት መመጣጥን አለመሆኑንም ሊያመለክት ይችላል!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*

x

Check Also

ብዙ ጊዜ እውነትን ውሸት ይቀድመዋል-የሺሃሳብ አበራ

ብዙ ጊዜ እውነትን ውሸት ይቀድመዋል፡፡ እውነት ዳተኛ ናት ወይም ቶሎ አትገለፅም፡፡ እውነት ቶሎ መገለፅ ባለመቻሏ ምክንያት በዓለም ...