አሁን ሀገሪቱ ያለችበት ሁኔታ ከ1966 ቱ አብዮትም ሆነ ከ 1983 ቱ የለውጥ ጊዜ ሁሉ የከፋ ነው| የሺሃሳብ አበራ

አሁን ሀገሪቱ ያለችበት ሁኔታ ከ1966 ቱ አብዮትም ሆነ ከ 1983 ቱ የለውጥ ጊዜ ሁሉ የከፋ ነው፡፡ ሃገሪቱ ፈርሷ በሌላ ቀለም እንድትሰራ በመዋቅር ደረጃ እየተሰራ ነው፡፡
….
ከትህነግ በስተቀር ሌሎቹ ሶስት አጋር ፓርቲዎች ከፍተኛ ፈተና ውስጥ ገብተዋል፡፡
..
ደኢህዴን

13 ዞኖች አካባቢ ያሉት የደቡብ ክልል 8ቱ የክልልነት ጥያቄ አንስተዋል፡፡አንዳንዶች የራሳቸውን ሰንደቅዓላማ በውስጥ እያዘጋጁ ነው፡፡ በደቡብ በአንዳንድ ዞኖች የፕሮቴስታንት ሃይማኖት መንግስታዊ ሃይማኖት እየሆነ ነው፡፡ለአብነት በወላይታ ዞን የህክምና ተቋማት ሳይቀር ከፕሮቴስታንት ውጭ አናክም እያሉ እንደሆነ ፍትህ መፅሄት አትታለች፡፡56 ብሄረሰብ ያለውን ደቡብን የሚመራው ደኢህዴን የህዝቡ ጥያቄ ፓርቲውን ቀድሞታል፡፡ ደኢህዴን ክልሉ ካቅሙ በላይ እየሆነበት ነው፡፡ የደቡብን መከፋፈል የትህነግም ሆነ አንዳንድ የኦሮሞ የፖለቲካ ሃይሎች ይፈልጉታል፡፡፡ትህነግ ብዙኃን ጠፍተው ንዑሳን እንዲኖሩ ትፈልጋለች፡፡ንዑሳን ለመዋጥም ለመቆጣጠርም ይመቻሉና፡፡
..
ኦዴፓ

ከኢህአዴግ አባል ፓርቲዎች መካከል ከኢህአዴግነት ያፈነገጡ የአዲስ እሳቤ ባለቤቶች ያሉበት ኦዴፓ ነው፡፡ የኦዴፓ አባላት በብዛት በትህነግ ኦነግ እየተባሉ ሲከሰሱ የነበሩ ናቸው፡፡ ነገር ግን ከኦህዴድነት ወደ ኦዴፓነት ስሙንም ግብሩንም የቀየረው ኦዴፓ በኦሮሞ ህዝብ ስነ ልቦና ዘንድ የኦነግን ያህል ቅቡልነትን አላገኘንም ፡፡ ኦነግ ልክ እንደ ሻዕቢያ ኢትዮጵያ የኦሮሚያ ቅኝ ገዥ ናት የሚል እሳቤውን ለወጣቱ ሲያስተምር ቆይቷል፡፡የኦዴፓ ደግሞ ኢትዮጵያን የኦሮሞ እናድርጋት እንጂ በወራሪነት አይመለከታትም፡፡ስለዚህ በሁለቱ ስብራቶች መሃል ልዮነቶች ተፈጥረዋል፡፡ ሸዋ እና አርሲ ከሞላ ጎደል ኦዴፓን ይደግፋል፡፡ምስራቅ ሀረርጌ፣ ምዕራብ ኦሮሚያ(ወለጋ) ፣ጉጂ አካባቢዎች የኦነግ ነፃ ቀጠና ሆነዋል፡፡ ሸኔ የሚባለው የኦነግ ክፍል ከወለጋ ተሻግሮ ወደ ቢሻንጉልም እያማተረ ነው፡፡ በነዚህ አካባቢዎች ኦነግ እስከ ዞን ያለውን ህዝብ እየመራ ነው፡፡ገንዘብም መዝረፉ አይቀርም፡፡
የኦሮሞ ፖለቲካ በሶስት ፅንፎች እንዲቆም በነጃዋር በኩል ሀሳብ ቀርቧል፡፡ ኢትዮጵያ የሚል ለዘብተኛ የኦሮሞ የፖለቲካ ድርጅት(እንደ ኦዴፓ ያሉት እና ሌሎች)፣አክራሪ ብሄርተኞችን ያቀፈ መገጠልን የሚደግፍ ፓርቲ እና የትጥቅ ድልን የሚደግፍ ፓርቲዎች ይደራጃሉ፡፡17 ቱም የኦሮሞ ፓርቲዎች በሶስቱ ስር ይመደባሉ፡፡ የኦሮሞ ሊሂቃን አንዳንዱ መገንጠልን ዛሬም ይፈልጋል፡፡ ብዙው ግን የኢትዮጵያን መልክ በመቀየር የኦሮሞ በማድረግ መኖርን ይመርጣል፡፡ ለዚህም በአንዳንድ በኦሮሚያ ክልል ባሉ ቤተክርስቲያናት ሳይቀር አረንጓዴ፣ቢጫ ቀይ ሰንደቃላማ ወርዶ በኦነግ እየተተካ ነው፡፡ የአብሲኒያን ጫና የኩሽ ኢምፓየር በመገንባት ኢትዮጵያን የኩሽ መንግስት እናደርጋታለን ብለዋል፡፡ለዚህ ስኬት ዓለም አቀፍ ተቋማትም እየሰሩ ነው፡፡በ 2008 የፕሮቴስታንት መፅሐፍ ቅዱስ ኢትዮጵያ የሚለውን ኩሽ ብሎ እንደተካው ይታወሳል፡፡ህትመቱ ጀርመን ስለሇነ በሁሉም አካባቢዎች ስለመሰራጨታቸው መረጃ የለም፡፡ ስለዚህ የደቡብ ብሄሮች ክልል መሆናቸው ብዙዎች በፕሮቴስታንት ሃይማኖት ኢትዮጵያን ኩሽ ብለው ይጠራሉ፡፡ የኢትዮጵያ መልክም ሙሉ በሙሉ ይቀየራል፡፡ አማርኛ ከስራ ቋንቋነቱ ይወርዳል፡፡ ሃገሪቱ የመቀጠሏ ሁኔታ አሳሳቢ ይሆናል፡፡ ከቀጠለች እንኳ የዛሬዋን መልክ ፈፅሞ አትይዝም፡፡

ትህነግ

ከሁሉም ፓርቲዎች የህዝብ ድጋፍ እና ታማኝነት አለው፡፡ህዝቡን አደራጅቷል፡፡ ተራው አርሶአደር የቡድን ዘመናዊ መሳሪያ አስታጥቋል የሚል መረጃም ይወጣል፡፡ ከ1989 ጀምሮ ኤርትራን ለመውጋት የሄዱ ከባባድ መሳሪያዎች ከትህነግ ጉያ አይጠፉም፡፡ ትህነግ ከማዕከላዊ መንግስቱ ብዙ የማያንስ ትጥቅ ይኖረዋል፡፡ ሀሳቡም ትጥቁም ስላለው መቀሌ ቁጭ ብሎ በ proxy war አማራን ሆነ ኦሮሚያን የግጭት ማዕከል ያደርጋል፡፡ ከገንዘብ እስከ ትጥቅ ሁሉም አለ፡፡፡ ሀገሪቱ ወደ ሙሉ ግጭት ብትገባ ትህነግ የተሻለ እድል ይኖረዋል፡፡
….
አዴፓ
….
አዴፓ ከ1972 ጀምሮ የመጣበት መንገድ አድክሞታል፡፡መንገድ ልቀይር ቢልም አልሆነለትም፡፡ አሁን ያለውን የሀገሪቱን ችግር የሚረዳው አይመስለኝም፡፡ አዴፓ ከ 1986ቱ ብአዴን በአሰራር እና በመዋቅር ብዙ አይሻልም፡፡ ኢትዮጵያን ለማጥፋት እና አዲስ መልክ ለመስጠት የሚደረገው ትግል ሁሉ ማረፊያው አማራ ክልል ነው፡፡ በአማራ ላይ ሁሉም ጠላት ሆኖ ይነሳል፡፡ ሁሉም ህዝብ በብሄሩ ተደረጅቷል፡፡ አማራ ገና ነው፡፡
አዴፓ ደግሞ የበለጠ ገና ነው፡፡ ነገሩ በጊዜው መፍትሄ ካላገኘ፣ክልሉ የብጥብጥ ማዕከል መሆኑ ገና ይቀጥላል፡፡
አዴፓ የሚመራው ህዝብ ተስፋ ስለቆረጠ
…ቢሮ የመንግስት ሰራተኛ ቀንሷል፡፡አንዳንድ ቢሮዎች ዝግ ናቸው፡፡በሆስፒታሎች ሳይቀር ሰራተኞች የማይገቡ አሉ፡፡ አዴፓ ምንም ቢል ምን የሚመራው ህዝብ ይጠረጥረዋል፡፡ ሳይታመኑ መምራት ከባድ ነው፡፡ ተከታይ ከሌለ መሪ የለም፡፡

አዴፓ ከመዋቅር እስከ አሿሿም አስተካክል ተብሎ ነበር ብዙ አልሰማም፡፡ ጥቂት ነገሩ የሚገባቸው አዴፓዎች ቢኖሩም በብዙኃኑ ጎታችነት ክልሉ እስኪፈርስ እያዮ ነው፡፡
….
ማዕከላዊ መንግስቱ

ማዕከላዊ መንግስቱ እንደ አዴፓ ደከም ያለ ነው፡፡ ከ 20 ሚኒስትር የትኛው የሃገሪቱን ችግር ተረድቶ ዘላቂ መፍትሄ እንደሚሰጥ እግዜር ይወቀው፡፡ ሰላም ሚኒስትር የሚባለው እንኳ የሃይማኖት አባቶችን ስብከት ከማሰበክ እና ተናጋሪዎች እየሰበሰበ ሰላም አስፈላጊ እንደሆነ ከመናገር የዘለለ ሚና አልተጫወተም፡፡ የጠሚዶ አብይ ካቢኔ ደካማ ነው፡፡ ጠሚዶ አብይም በየአካባቢው ያለውን ስብራት ለመጠገን ጉልበት ሳያንሳቸው አይቀርም፡፡ በእርግጥ ሃይላቸውን ትህነግ ያጠፋውን በማከም አባክነዋል፡፡ ግን ከጣፋጭ ንግግር ያለፈ ለነገ ሀገሪቱ ሰላም ዋስትና የሚሆን ነገር ያላቸው አይመስልም፡፡

በሀገሪቱ የማህበራዊ ቀውስ ስለተጋረጠ ተፎካካሪ ፓርቲዎች አይስማሙም ፡፡ሀገሪቱ እየሞተች እርስ በእርሳቸው ለመጠላለፍ ይተጋሉ፡፡ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ከሰባዊነት ርቋል፡፡ይህ ደግሞ ሀገሪቱን የበለጠ ይጎዳታል፡፡
….
እንደ አማራ፡
እዚህ ፊስቡክ ላይ የማይነገሩ ብዙ ስጋቶች አሉ፡፡ አንደኛው በጎንደር የተጀመረው ነው፡፡ሶስቱ አብንም ሆነ አዴፓ፣አክቲቪስቱም ሆነ ሌላው ሊሂቅ ተባብሮ ከሰራ ሊያመክናቸው ይችላል፡፡ አማራን የማጥፋት ዘመቻ በመዋቅር እየተሰራ ነው፡፡ ጎንደር አንድ ዞን በአንድ ወር ብቻ ከ 1200 ቤት በላይ ተቃጥሏል፡፡ ብዙው ተፈናቅሏል፡፡ይህ አማራ ከራሱ መሬት ላይ እንዲህ የሚሆነው፡፡
ይህ ገና ትንሹ ነው፡፡ ይቀጥላል፡፡ለምን? ዝርዝሩ አይነገርም፡፡

አሁን አማራ የመኖር እና ያለመኖር ስጋት ውስጥ ነው፡፡፡ ስለዚህ ሁሉም አማራ በአንድ ላይ ቁሞ አዴፓን መደገፍ፣አብን መደገፍ፣የመንግስት መዋቅራትን መደገፍ ያስፈልጋል፡፡
ሰላም በጣም የሚያስፈልግበት ወቅት ነው፡፡ የበለጠ ለመደራጀት፣የበለጠ ችግሮችን ለመለየት እና መፍትሄ ለመስጠት ሰላም ያስፈልጋል፡፡ አብን ከፊስቡክ ጫጫታ ወጥቶ መሬት ላይ ይስራ፡፡ ፓርቲ በፊስቡክ አይመራም፡ አዴፓ እና አብን የበለጠ ይገናኙ፡፡በጋራ ይስሩ፡፡ የአማራ ወጣቶች አደረጃጅት ይቀናጁ፡፡ይናበቡ፡፡

x

Check Also

የአማራ ክልል ከፍተኛ የፀጥታ ክትትል ችግር አለበት – ሚኪ አማራ

⚡️ክልሉ እንደ ሃብታም ቤት ተበርግዶ (የሃብታም ቤትስ አንዳንዴ ይዘጋል) ሲፈልግ ከባድ መሳሪያ፤ ሲፈልግ ታንክ ፤ሲፈልግ ...