የዛሬው ራያ፤ የቀድሞው አንጎት አውራጃ እስከ አሸንጌ ሐይቅ ድረስ የወሎ ክፍል እንጂ የትግራይ ….

የዛሬው ራያ፤ የቀድሞው አንጎት አውራጃ እስከ አሸንጌ ሐይቅ ድረስ የወሎ ክፍል እንጂ የትግራይ አካል አይደለም፤ አልነበረምም!

(አቻምየለህ ታምሩ)

በቤተ ወያኔ መቼም እሳ ብሎ ነገር የለም። ጊዜ የሰጠው ቅል ድንጋይ ቢሰብር፤ ፋሽስታዊ አገዛዛቸውን የዘላለም ርስት አድርገውት ከተግባራዊነቱ በመለስ ምንም ያልቀረውን የአገራቸውን የታላቋ ትግራይ ሪፑብሊክን ደቡባዊ ድንበር አሸንጌን አልፈው አንጎትን [ሰሜን ወሎን] ዘልቀው እስከ አለውሀ ድረስ ለማማተር ይቃጣቸዋል። ካለፉት ሁለት ወራት ወዲህ ከአድዋ የመጡ ትግሬዎች በራያ ልጆች ላይ ጦርነት ከፍተው ነባሩን የአማራ ሕዝብ ትግሬነትን ካልተቀበልህ እያሉ በማፈንና በመግደል እያፈናቀሉት ይገኛሉ።

እስቲ የትግራይን ደቡባዊ ክፍልና የቀድሞው አንጎትን [ የዛሬው የወሎን ሰሜናዊ አካል] በሚመለከት ዶሴው ይውጣና ይመርመር።

ከታች የታተመው ካርታ በ15ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ታሪካዊውን የአንጎት አውራጃ የሚያሳይ ነው። ታሪካዊው የአንጎት አውራጃ ከትግራይ በስተ ደቡብ በኩል ይገኝ የነበረና አሸንጌ ሐይቅን አጠቃልሎ ባብዛኛው ዛሬ ራያ [ቆቦ + አዘቦ] ተብሎ ዛሬ የሚጠራውን የሰሜን የወሎ ክፍል የሚያቅፍ ግዛት ነበር። ካርታው ለመጀመሪያ ጊዜ የተዘጋጀው ፔትሮ ዴል ማሳዦ በሚባል የፍሎሬንስ [ጥሊያን] ውስጥ ይኖር በነበረ የታሪክ አጥኝና የካርታ ባለሞያ እ.ኤ.አ. በ1452 ዓ.ም. ነው።

የታሪክ ጥናቱና የካርታ ዝግጅቱ የተካሄደው በዐፄ ይሥሓቅ እና በዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ኢትዮጵያን ከጎበኙት የአራጎኑ ንጉስ አልፎንሶ 5ኛ መልዕክተኞች፤ ኢትዮጵያን ጎብኝተው ከተመለሱ የአገሩ ነጋዴዎች፣ ተጓዦች ፣ የቫቲካን አስተማሪዎችና በፍሎሬንስ በስደት ይኖሩ ከነበሩ የኢትዮጵያ መነኩሳት ማስረጃና መረጃ በመሰብሰብ ነው።

ካርታው ዛሬም ድረስ በቫቲካን የሚገኝ ሲሆን እ.ኤ.አ. በ1955 ዓ.ም. በካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ አሳታሚነት Osbert Guy Stanhope Crawford በሚባል የአርኪዮሎጂ ባለሞያ ተዘጋጅቶ «Ethiopian Itineraries, Circa 1400–1524: Including Those Collected by Alessandro Zorzi at Venice in the Years 1519–1524» በሚል ርዕስ በታተመ መጽሐፍ ገጽ 13፣ 14 እና 51 ውስጥ ይገኛል።

በካርታው መሰረት ዛሬ «ትግራይ ክልል» እየተባለ በሚጠራው የወያኔ ግዛት ውስጥ የሚገኝው የአሸንጌ ሐይቅ የአንጎት አካል ነው። ይህ ማለት በግፍ ወደ ትግራይ ክልል የተጠቃለለው የአሸንጌ ሐይቅ ያረፈበት መሬት አንጎት አውራጃ እንጂ የትግራይ አካል አይደለም ማለት ነው። ታሪካችን በመዝገብ መግባት ስላለበት፤ ነገ ሌላ ቀን ነውና አይደለም ዛሬ የሚመኙት አለውሀ አሸንጌ ሐይቅ ራሱ የሰሜን ወሎ አካል የአንጎት ክፍል መሆኑን ትውልዱ ሁሉ ሊያውቅ ይገባል እንላለን።

አገርና መንግሥት ካለ በማንነታቸው መጠራት በመፈለጋቸው ብቻ የለም መሬት ጥማቱን ለማርካት ሲል ወረራ በማካሄድ የነገድ ጭቆናና ጦርነት አውጆ ንጹሐን የአንጎት ልጆችን እየጨፈጨፈ ያለውን ፋሽስት ወያኔን እንደዚህ አይነት ዶሴዎች እያሉ እጁ በፍጥኝ ታስሮ ለፍርድ እንዲቀርብና እየፈጸመው ላለው የዘር ማጥፋት የእጁን እንዲያገኝ ማድረግ ይቻላል!

x

Check Also

አዴፓ የለውጡ ለኳሽ እና ጉልበት – ሚኪ አማራ

በመጀመሪያ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እንኳን ለአንደኛዉ አመት በአል አደረሰዉ እላለዉ፡፡ በመቀጠል የአቶ ገዱ የመቀሌ እና ጎንደር ...