የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ (አዴሃን) ታጋዮች ወደ ኢትዮጵያ ገቡ፣ በየከተማው ደማቅ አቀባበልም ተደረገላቸው

የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ (አ.ዴ.ሃ.ን) ትግሉን በሰላማዊ መንገድ ለማካሄደ ወደ ኢትዮጵያ ገባ!

የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ (አ.ዴ.ሃ.ን) በአማራው ላይ የሚፈፀመው እጅግ ዘግናኝ ግፍ በአስገደዳቸው እውነተኛና ቆራጥ የአማራ ልጆች በ 2002 ዓ.ም የተቋቋመ ድርጅት ነው፡፡ አ.ዴ.ሃ.ን የአማራው የብዙ አመታት የህልወና፣ የፍትህ፤ የዴሞክራሲ፤ የእኩልነትና የአንድነት ጥያቄ ለማረጋገጠ መቀመጫውን በኤርትራ በርሃ አድርጎ የወያኔን መንግስት ይሽም ቅጊያን ጨምሮ በተለያዮ የትግል ስልቶች የወያኔን መንግስት ሲፋልም ቆይቷል፡፡

ካለፉት 3 ወራትና ጠቅላይ ምንስቴር ዶ/ር አብይ ወደ ስልጣም ከመጡ ወዲህ በኢትዮጵያ ያለው ለውጥ በመገምገም በቅርቡ በሰላማዊ መንገድ አገር ቤት ገብቶ ለመታገል የወሰነው የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ (አዴሃን) ወታደሮች ከኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ በዛሬው ቀን ገብተዋል። የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ (አ.ዴ.ሃ.ን) ከኤርትራ በረሃ ኦማህጀር በመነሳት ወደ አማራ እርስት ከሆነችው ሁመራ ከተማ በመግባት ጉዞውን ወደ ባህርዳር አድርጉአል። የአዲሃን ታጋዮች ባለፉባቸው የአማራ ከተሞች ማለትም በዳንሻ ፣ በሶሮቃ፣ በጎንደር እና ሌሎች ከተሞች ላይ የከማው የአማራ ህዝብ በመውጣት ደማቅ አቀባበል አድርጎላቸዋል።

የቀድሞዉ የአርበኞች ግንባር የዉጭ ጉዳይ እና የፖለቲካ ጉዳይ ሀላፊ ሆኖ ለረዥም ጊዜ የሰረዉ፣ በአርበኞች ግንቦት ሰባት የህዝባዊ እምቢተኝነት መምሪያ እና የፖለቲካ ሀላፊ የነበረዉ፣ እና አዴሀን ነህ በሚል በግንቦት ሰባት አመራሮች ትዕዛዝ በእስር ስቃይ ላይ የነበረዉ ጀግናዉ ወንድማችን መንግሥቱ መንግስቱ ወልደስላሴ ከብዙ የእስር ስቃይ በኋላ ተፈቶ የአዴሀንን መኪና እያሽከረከረ የተከዜን ድልድይ ያቋረጠዉ እሱ ነዉ፣ ከአዴሀን ሰራዊት ጋር አብሮ ወደ አግሩ ገብቷል!!

የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ (አ.ዴ.ሃ.ን) ወደ ኢትዮጵያ ሲገቡና በየከተማው ሲገቡ ህዝቡ ያደረገላቸውን አቀባበል የሚያሳይ ቪዲዮ

የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ (አዴሃን) ከኤርትራ በረሃ ኦማህጀር በመነሳት ወደ አማራ እርስት ከሆነችው ሁመራ እየገቡ ነው

የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ (አዴሃን) ከኤርትራ በረሃ ኦማህጀር በመነሳት ወደ አማራ እርስት ከሆነችው ሁመራ እየገቡ ነው

የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ (አዴሃን) ከኤርትራ በረሃ ኦማህጀር በመነሳት ወደ አማራ እርስት ከሆነችው ሁመራ እየገቡ ነው

የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ (አዴሃን) ወደ ኢትዮጵያ ሲገቡ

x

Check Also

ከሶማሌ ክልል የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆች የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ – በላይነህ አለምነህ

ከሶማሌ ክልል የተፈናቀሉ የአማራ ተውላጆች የተቃውሞ ሰልፍ በባህርዳር ከተማ እየተካሄደ ነው ። በማንነታቸው የተነሳ ከሶማሌ ...