ሰበር ዜና | ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ የጋሞ ብሄር ተፈናቃዮችን ለመጎብኘት ሄደው ሳያገኟቸው ተመለሱ

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከአዲስ አበባ ዙሪያ ተፈናቅለው በመዳኒአለም ትምህርት ቤት የሚገኙ የጋሞ ብሔር ተወላጆችን ለመጎብኘት ቢሄዱም ከተፈናቃዮች በደረሰባቸው ተቃውሞ ቦታውን ለቀው መሄዳቸው ታውቋል፡

በህዝባችን ላይ የደረሰው በደል ትልቅና የዘር ማጥፋት ቢሆንም ድርጊቱን የፈጸሙ ወገኖች ጽንፈኞች፣ የአንቀጽ 39 አቀንቃኞችና፣ በጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ እየመጡ ያሉ የለውጥ ሂደቶችን ጭምር የማይቀበሉ ጸረ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት አቋም ያላቸው የሽብር ቡድኖች ናቸውና በአዲስ አበባ በተለያዩ መጠለያ ቦታዎች ላይ የምትገኙ ተፈናቃይ ወገኖቻችን በቀጣይ ጊዜያቶች ውስጥ በጠቅላይ ሚንስትር የሚወሰዱ ርምጃዎችን በተጨማሪም በጋሞ ብሔረሰብና በአርባምንጭ ከተማ ላይ ያላቸውን አቋም እስክናይ ድረስ ለጊዜው ከስሜት በመውጣት ታስተናግዷቸው ዘንድ በተሰበረ ልብ ውስጥም ብንሆንም ወገናዊ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን!!!

ናቶ /የጋሞ ወጣቶች ዓለም አቀፍ የነፃነት፣ የፍትህ፣ የእኩልነት፣ እና የዴሞክራሲ ንቅናቄ ህብረት/

ድል ባለፉት ጊዜያቶች በፍትህ፣ በዲሞክራሲ፣ በልማት፣ እና በመልካም አስተዳደር እጦቶች ሲሰቃይ ለቆየው ለጭቁኑ ለጋሞ ህዝባችን!

ምንጭ: ናቶ የጋሞ ወጣቶች ንቅናቄ ህብረት

x

Check Also

ከሶማሌ ክልል የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆች የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ – በላይነህ አለምነህ

ከሶማሌ ክልል የተፈናቀሉ የአማራ ተውላጆች የተቃውሞ ሰልፍ በባህርዳር ከተማ እየተካሄደ ነው ። በማንነታቸው የተነሳ ከሶማሌ ...