ዶር አብይ እና ሚኒሶታ – ወንድይራድ ሃ/ገብርዔል : ክፍል ሦስት

ሚኒሶታን ትንሿ ኦሮሚያ ይሏታል። አሜሪካ ውስጥ ከሚገኙ ግዛቶች በቁጥር በርከት ያሉ ኦሮሞዎች የሚገኙት ሚኒሶታ ነው። ዲሲን የታማኝ በየን ግዛት እንዳልናት ሁሉ ሚኒሶታንም የጅዋር ሞሃመድ ዕቁባት ናት ብንል ስህተት አይመስለኝም። ለነገሩ ተቅርብ ጊዜ ወዲህ ድምጣቸው ጠፍቶ እንጅ በቁጥር በርካታ ትግሬዎችም የሚኖሩት በዚሁ በሚኒሶታ ነው። ቁጥራቸው ሚዛን ባይደፋም አማሮችም ሚኒሶታ ውስጥ ይኖራሉ።

ሚኒሶታና ዶ/ር አብይ የነበራችዉ ቆይታ በእዉነት ያደናግራል። “እንዲህ ሆኖ እንዲያ ሆነ” ብሎ ለመታዘብም ሆነ ለመናገር ትንሽ ያስቸግራል። ተጀመረ ሲባል፡ በውል ሳይጀመር፡ እየተጨረሰ  … ተጨረሰ ሲባል ደግሞ፡በውል ሳይጨረስ እየተጀመረ ሚኒሶታ ላይ የተቋጠረው ሳይፈታ፣ የተገነባው ግንብም ሳይፈረስ፡ የድልድዩ ግንባታም ሳይጀመር ሚኒሶቶች ዶር አብይን በብራ ሸኝተዋቸዋል። በእውነት ያሳዝናል። ዶር አብይም አዝነዋል። እረ የተናደዱም ይመስላል። “ጅሩ ጅሩ እያላችሁ እንዲህ ታዋርዱኝ” ያሉም ይመሰላል። ከማዘናቸው የተነሳ በአዘጋጆቹ (በነጅዋር) ሰም አማራን ይቅርታ እስከመጠየቅም ደርሰዋል። ደስ ደስ የሚሉ የዛሬ ፍሬዎች የነገ አበባዎች የሆኑ ህጻናት የብሄር ብሄረሰቦችን ባህላዊ ዘፈን ሲያቀርቡ የአማራ ባህላዊ ዘፈን ሳይቀርብ በመቅረቱ ጠቅላይ ሚንስትሩ ደብሯቸዋል። ለነገሩ ቢደብራቸው አይፈረደም። መቸም የአማራ ባህላዊ ዘፈን ተረስቶ ሳይቀርብ ቀረ መባል የሚቻል አይመስለኝም። ጋንቤላው፣ ሱማሌው፣ ትግሬው፤ አፋሩ … ይሄ ሁሉ ሳይረሳ 50 ሚሊዮን አማራ በምን ሂሳብ ተረሳ ይባላል?። ተረሳስ ማለት አይቻልም። እመብርሃን ምስክሬናት እንደዛ ሊባል አይችልም። አይባልማ!።  እንግዲህ ይህንንም የህዎሃት ስራ ነው ትሉት ይሆናል። አይደለም!  እንዲህ ያለው ሸር ግጥም አድርጎ የነጅዋር ነው። የጠቅላይ ሚንስትሩ ባለቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸውም ጭምር በሁኔታው እንደምታዝን እገምታለሁ። እንዴ! ታዝናልች እንጅ እንዴት አታዝንም? አይይይ!  እነጅዋር ክፉ ሰዎች ናቸው። እስኪ ምናለ ለዝናሽ ሲሉ አንኳ እንዴያው ለአንዲት ደቂቃ “አረሱትን!” ቢያዘፍኑላት ኖሮ? መቸስ ቢሆን ተዋልዳ ተካብዳ ከነሱ እንደአንደኛው የሆነ ፍሬ አፍርታ አልነበረም? … ልጆቿ እኮ በስንጥቅ አኦሮሞዎች ናቸው። ጅዋርስ ቢሆን ከፉው ስንጥቅ ሆኖ እንጅ ያው ስንጥቅ አሮሞ አደል? በነገራችን ላይ ሸረኞቹ ስንጥቆቹ ናቸው። እነ ጸጋየ አራርሳ። የድሮዎቹ ስንጥቆች ቅንና ሃገር ወዳዶች ነበሩ። እነ ሎሬት ጸጋየ ገብረመድህን። እነጥላሁን ገሰሰ። ኧረ ብዙ ናቸው።

አረሱት” ለዝናሽ ሲያንሳት ነው። ፋሲል ደመወዝስ ቢሆን ድምጹ ቢሰማ ምን ነበርበት። “ሸሸ ሸሸ አብይ እሸሸ … ሸሸ ሸሸ ለማየ እሸሸ!”። ለካስ የማህጸን ብቻ ሳይሆን የዘፈንም ዥንጉርጉሪት አለው። “እሽሽ እሽሽ አብይ እሽሽ … ለማየ እሽሽ እሽሽ … አረሱት! አረሱት! ያውላችሁ ልቤ ተከፋፈሉት”። ዥንጉርጉሪት።   አየ ፋሲል!

 “አረሱት …  አረሱት …

 ያውም የኛን መሬት …. ያውም የኛን እጣ

እነርሱ ምን ያርጉ  …..  ከኛ ሰው ሲታጣ”  ….  እናዳላለ? …. ጓንዴውን ይዞ ታችና ላይ አርማጭሆ፡ ወልቃይት ጠገዴ፡ ፍየል ቆለጥ ተራራው ላይ ጉኒን በሎ ጠብመንጃውን እያናገር ሲጎማነን ነበር ፋሲል የሚያምርበት። መቸም ፋሲል ሽል አልቀየረም። ዲስ ክፉ አገር ነው። መቸስ ሌላ ምን እነላለን።

ዶር አብይ ዲሲ እና ሎሳንጅለስ ላይ ያተርፉትን ጨምሮ ሚኒሶታ የሆነው ሁሉ አክስሯቸዋል። እንደ ሰው አሳዝነውኛል። ጅዋር ያንሁሉ ድካማቸውን በሰአታት ውስጥ ትቢያ ውስጥ ደባለቀው። የዶ/ር አብይን እረፍት አልባ ድካም ሳስብ ዶ/ር ነጋሶ ላይ የሆነው ትዝ አለኝ። ከነዶክተር መርሻ ገዳሙ ጋር በዋና አዝጋጅነት የምሰራባት መፅሄት ነበረች። በዝች መፅሄት ውስጥ “ምርጥ የዘፈን ምርጫ” የተሰኘች አምድ ነበርችን። ከርዕስ አንቀጹ በተጨማሪ ይችን አምድ የምሸፍናት እኔ ነበርኩ።  ታዲያ… ወቅቱ የቀደሙት የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ዶር ነጋሶ ጊዳዳ ከአቶ መለስ ጋር ተጣልተው ከድርጅቱም ከመንግስት ስልጣንም የተወገዱበት (የለቀቁበትም ሊሆን ይችላል) ወቅት ነበር። ዶ/ር መርሻ ደወለና “እባክህ ለዶር ነጋሶ እና ለአቶ መለስ ዘፈን ምረጠላቸው” አለኝ። ምንገዶኝ አልኩና ለሁለቱም እንዲህ መርጥኩላቸው።

                       “ፍቅሯን እንደ አርቂ …. ሶስት ጊዜ ቀምሸ፤

                        ኮቴን ጥየ ሄድኩኝ …..  ሱሪየን ለብሸ”።   መራጭ  ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ለአቶ መለስ ዜናዊ

          =================== —————— ====================== ——————–

                      “አሮጌ ቆርቆሮ  …  አያገለግልም፤

                       ሂጅ ወደናትሽ …  የወለደ አይጥልም”።    መራጭ አቶ መለስ ዜናዊ ለዶ/ር ለጋሶ ጊዳዳ

መለስ ነጋሶን እንዳደረገው ሚኒሶቶች ዶ/ር አብይን ኮቱን አስጥለው ያለግጣም ሱሪ ልከውታል። እኔማ ቢጨንቀኝ አንድ ነገር አስብኩ። “ይሄ ሰውየ እንደሚባለው አማራ ነው እንዴ?” እየተሰኘው በራሴ ላይ ቀለድኩ። አደለም እኮ። እንዲያው እኔን ለሱ ጨንቆኝ እንጅ። አማራ እኮ ሰው ያለአግባብ ሲበደል አይወድም። ይሄን ሰውየ ሚኒሶቶች ያለአግባብ በድለውታል። እኔም ያለአግባብ አዝኛለሁ። ክፉ በሸታ ነው። ለራሴ የአማራነት ዋስተና የለኝ ሰው ሚኒሶታ ለመደመር ሄዶ ተቀነሰ ብየ አዝናለሁ። ይሄ ቅሌት ነው። ቅሌታም ሃዘን። አልኩና ከሃዘኔ ተጽናናው።

 ሚኒሶታ የሆነው አንዳንዱ ነገር ደግሞ እጅግ እጅግ አስደንጋጭ ነበር። ትንሽም ያሰፈራል። የአሜሪካ የአማርኛው ድምጽ አማርኛው ቋንቋ አገልግሎት ባልደረባ ሶሎሞን አባተ ከአንዲት ዘጠኝ አመት የሆናት የምታምር ኦሮሞ ህጻን ልጅ ጋር ያደረገውን ቃለ-ምልልስ ሳዳምጥ ለደቂቃዎችም ቢሆን ፈዝዠ ነበር።

ሶሎሞን  …..  ዕዚህ ለምን መጣሽ

        ህጻኗ   ……   ዶር አብይን እንኳን ደህና መጣህ ለማለት። አሁን  በጣም በጣም ደስተኛ ነኝ፤ ምክንያቱም ትግሬ የኛን

                       ኦሮሞዎች ቶችቸር እይያደረገ ነበር።

 ሰሎሞን  …. (አቋረጣትና) … አደለም! ይሄ ነገር ስህተት አይመስልሽም? አላት። ትግሬ ኦሮሞን ቶርቸር አላደርገም። ሂጅና

      ቤተሰቦችሽን እንደገና ምን እንደተደረገ፡ ምን እየተደረገ እንዳለም ጠይቂያቸው፡ እሽ። ለመሆኑ ስንት አመትሽ                    ነው?

       ህጻኗ ……  ( በጋዜጠኛው መልስ መናደዷ ፌቷ ላይ ይነበባል) … (በግድ ተገልግላ መልስ ሰጠች).. ዘጠኝ ።

ይሄ ትንሽ ከበድ ያለ ነው። ሚኒሶታ ላይ እንዳየነው ከሆነ ብራኬቱ ፈረሰም አልፈረሰም መደመር እጅግ ፈተና መሆኑን ነው።

 ቢሆንም ግን!  ፑፍ! ፑፍ! አለ ዘአብ። ጅዋር ጨካኝ ሰው ነው። ዘአብ የልጅነት ጓዴ ነበር። በታሪካዊው እና ታላቁ ትምህርት ቤት ዳግማዊ ቴውድሮስ አጅባር ስንማር እኔና ዘአብ አንድ ወንበር ላይ ነበር የምንቀመጠው። የዘአብ አባት አቶ ብርሃነመስቀል የደብረታቦር መብራት ሃይል አገልግሎት ዋና ስራ አስኪያጅ ነበሩ። የሚኖሩትም እዛው የባለሰልጣኑ ግቢ ውስጥ ነበር። ዘአብ አባቱ ለስራ ተቀየር እና ወደአዲስ አበባ ሲሂድ ከቤተሰቡ ጋር ደብረታቦርን ለቀው አዲስ አበባ ገቡ። የምወደው ዘአብ የልጅነት ጓዴ ጥሎኝ ሲሄድ ምርር ብየ አለቀስኩ። በእውነት በጣም አዘንኩ። ቢሆንም አንድ ቀን አዲስ አበባ ስሄድ አገኘው ይሆናል በሚል ተጽናናሁ። ምኞቴ ሰመረና አዲስ አበባ ለትምህርት የመሄድ እድል ሳገኝ ዘአብን አፈላልጌ አገኘሁት። ያን ግዜ መንግስት ተቀይሯል። የዘአብ ዘመዶች የምኒሊክ ቤተ መንግስት ውስጥ ገብተዋል። የዘአብ ባህሪም እንደመንግስቱ ተቀሮ አገኘሁት። በጣም ደነግጥኩ:: ልቤ በሃዘን ተሰበረ። “እውነት አንተ የልጅነት ጓዴ ዘአብ ብርሃነመስቀል ነህ?” ስል ጠየኩት። “አዎ” አለኝ። በአግራሞት ትንሽ ካወራሁት በኋላ “የአማራነት ሰነልቦና ጭናችሁ ማንነቴን ጨፍልቃችሁ…… “ ሲለኝ፤ ሳልሰናበተው ጥየው ሄድኩ። የነዘአብ ነገር የበቃኝ ያነዕለት ጀምሮ ነው። ዘአብ ዛሬ ሰዊድን ሃገር ይኖራል ሲባል ሰምቻለሁ። የዶር አብይ ነገር!  ሰለዶክተር አብይ ለመጻፍ ሲነሱ በዙ ነገር ይታወሳል። እናም እንደዋልካ እርሻ ብዕርን ከወዲያ ወዲህ ያሰረግጣል።

 ዶ/ር አበባ ፍቃዴ ግን የሚሰማት ካገኘች ዛሬም እየተናገረች ነው። “አብይ ማዘናጊያ ነው ትላለች”። “ተቀዋሚ የሚባለውም ሽንፊላ ነው ባይ ናት፡ አብይ ተቃዋሚውን ንቆታል” ነው የምትለው። በተለይ የዲሲዎቹን የዶ/ር መንጎች አላተረፈቻቸውም። ዶር አበባ ጠንካራ ሰው ነች።  እዚህ ላይስ እዉነቷን ነው እኔም እጋራታለሁ። ተቃዋሚው አጀንዳ የለውም። ለጭብጨባ ብቻ የተጋ ተቃዋሚ ነው። ዶ/ር አበባ ምርጥ አማራ ናት። ተደራጅታ መታገል ግን ምርጫዋ አደለም።  በአንድ አጋጣሚ ዶ/ር አበባ እኔን፡ ዑመር መሃመድን እና አምደጽዮንን ሰለአማራ ህዝብ ስነልቦና ተከታታይ የሆነ በሳምንት አንድ ግዜ ማክሰኞ ማኽሰኞ ትምህርት ትሰጠን ነበር። ብዙም አላስደሰትናትም መሰል፣ ስነልቦናችን እንደገለባ ሸክም ቀለለባት መሰል ቀስ አድርጋ ተሰወረችብን ወይ እኛ ተሰወርንባት። ቢሆንም በጣም ነው የምንወዳት። እርሷም አትጠላንም። እንደኢሃፓው ዘመን ወጣት ተንኮለኞች ልንሆንላት ግን አልቻልንም። ሞክረን ነበር። ከየት አናምጣው።

ለማንኛውም ዶ/ር አብይ ፓትሪያሪክ መርቆርዮስን ይዘው ወደ ኢትዮጵያ ዛሬ ይመለሳሉ። በእውነት ትልቅ ሰራ ነው የሰሩት። የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም የተዋህዶ አማኙ ከእውነተኛው ፓትርያሪክ ጋር ዛሬ ይገናኛል።

ስብሃት ለእግዚአብሄር!

x

Check Also

የአማራ ክልል ከፍተኛ የፀጥታ ክትትል ችግር አለበት – ሚኪ አማራ

⚡️ክልሉ እንደ ሃብታም ቤት ተበርግዶ (የሃብታም ቤትስ አንዳንዴ ይዘጋል) ሲፈልግ ከባድ መሳሪያ፤ ሲፈልግ ታንክ ፤ሲፈልግ ...