የአማራ ህዝብ ያበጠ ዝና ያላቸውን ሰዎች ይከተል ወይስ ባለዝናዎቹ የአማራን ህዝብ ይከተሉ ?

የአማራ ህዝብ ምድር ላይ መኖር ከጀመረ ጊዜ አንስቶ እስካሁን ድረስ እጅግ አስከፊ የሚባል ህይወትን እየገፋ ይገኛል። ድል ሲያደርግ ፣ ድሉን ሳያጣጥም ሌላ እንቅፋት ፊቱ ላይ ሲደቀን የመጣበትን መከራ ለማሸነፍ መላ ሲዘይድ ሲሞክር፣ ሲወድቅ ሲነሳ 21ኛው ክፍለ ዘመን ላይ ደርሷል። በዘመናዊ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ የአማራ ህዝብ የፖለቲካ አስኳል የአንድነት እና ሁሉን አሳታፊ ፖለቲካ አመለካከት ነበር። በዚህ አመለካከቱ ኢትዮጵያ የምትባል አንድት የተለያዩ ጎሳዎች የሚኖሩባት አገር ለመፍጠር ከፍተኛ መስዋእትነት ከፍሏል። እየከፈለም ይገኛል። ለበርካታ አመታት ባካሄደው ሁሉን አቀፍ የፖለቲካ አካሄድ ራሱን አጥቷል። አገር እመስርታለሁ ብሎ አማራነትን አዳክሟል፣ የአማራን እሴቶች አውድሟል፣ አማራን በኢኮኖሚ አድቅቋል። የመጨረሻ ድምር ውጤቱም ውድቀት በሚል ተደምድሟል። ከዚህ የተማሩ አንዳንድ የአማራ ልጆች አማራ ከመነሻው ሀ ብሎ መጀመር አለበት አሉ። ፕሮፌሰር አስራት አማራ ብለው ድርጅት መሰረቱ፣አደራጁ። ፈተናው ቢከብዳቸውም ወደኋላ ሳይሉ አላማቸውን ላማስቀጠል የህይወት መስዋእትነት ከፈሉ። የሳቸው የትግል አላማ ግን መቀጠል አልቻለም ነበር። በርካታ የአማራ ልጆች መልህቁ በጠፋበት የአንድነት ፖለቲካ ሲታመሱ ፣ሲተራመሱ ፣ ወድቀው ህዝቡን እየጣሉት ዛሬ ድረስ ዘለቁ። ሆኖም ከበርካታ አመታት በኋላ የአማራ ወጣቶች የታላቁን አባታቸውን ራእይ አንግበው ተነሱ። አማራ የሚድነው ሀ ብሎ በማንነቱ ሲደራጅ እና በአማራነቱ ጥቃት እየተፈጸመበት እንደሆነ ተገንዝቦ በአማራነቱ አንድ ላይ ቆሞ ሲከላከል ነው አሉ። የአማራ ሞት እና ውድቀት የማያመው ሃሳዊው የአንድነት ጎራ የሚያዘንብባቸውን የጥላቻ እና የስም ማጥፋት ዘመቻ ተቋቁመው አማራን አነቁ። የአማራ ህዝብም እራሱን አወቀ። ለበርካታ አመታት የሄደበት ፖለቲካ መንገድ ውድቀትን ቢያከናንበውም ከ3 ወይ 4 አመት ያልበለጠው ትክክለኛ የትግል መስመሩ በሚገርም ፍጥነት ተስፋ ሰጭ ለውጥ አመጣለት። ለራሱ የሚጠቅመው ደረጃ ላይ ባያደርሰውም ጠላቶቹን ለመጣል ግን አስችሎታል። ትክክለኛ መንገድን ስትከተል ውጤቱ ጊዜ አይፈጅም። የሆነ ሆኖ አሁን የአማራ ህዝብ ማንን ይከተል የሚለው ግን መልስ አላገኘም። አስተሳሰብን ወይስ ግለሰብን ? ወደውጤት የሚያደርሰውን አመለካከት ወይስ ያበጠ ስብእና የገነቡ አንዳንድ አማሮችን እና አማራ መሰሎችን ? መልሱ ቀላል ነው። መልሱ መሆን ያለበት በአጭር ጊዜ ለውጤት የሚያበቃውን አስተሳሰብ እና የፖለቲካ መርህ መከተል ያለበት ነው። የአማራ ህዝብ መከተል ያለበት በአፋጣኝ ለውጤት የሚያደርሰውን የአስተሳሰብ መስመር ነው። እሱም የአማራ ብሄርተኝነት ነው። የገነነ ግለስብዕና ግን የተሳሳተ አመለካከት ያላቸውን ሰዎች ተከትሎ ነጻ መውጣት እንደማይቻል ያለፉት 100 አመታት ፖለቲካችን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። ዝና  እና ስኬት የሚገናኙ ነገሮች አይደሉም። እንደህዝብ የጥበብ (Wisdom)  ምንጭ እና የጥበብ ተከታዮች እንጅ የዝና ማህበረሰብ ወይም በዝና የሚጎተት ህዝብ መሆን የለብንም። ሌላውን ትቶ ከአጼ ሚንሊክ ዘመን ጀምሮ እስከዛሬዋ ቀን ያለውን የፖለቲካ ትርምስ ሰከን ብሎ ላሰናሰለው ለአማራ ህዝብ የነጻነት ጉዞ የሚያዋጣው መንገድ የቱ እንደሆነ ቁልጭ ብሎ የሚታይ ገሃድ ነው። ሆኖም የአማራ ህዝብ መዳኛ የትግል(አደረጃጀት) መስመር ከታዋቂ ግለሰቦች ጋር ከተምታታብን ውድቀታችን አፍንጫችን ላይ መሆኑ ይታወቅ። የምንከተለው አስተሳሰብ ነው ወይስ የግለሰብ ስም ? ለዚህ ጥያቄ አማራ ሁሉ ቁርጥ ያለ መልስ መስጠት አለበት። ይህ ካልሆነ እጅግ ፈታኝ ችግር በቀናት ውስጥ ይገጥመናል። አሁን ባለው ፈታኝ ወቅት የአማራ ህዝብ አይደለም ታዋቂ ሰዎችን መከተል ያለበት። ታዋቂ ሰዎች ናቸው የአማራን ህዝብ የትግል መስመር አምነው መቀበል እና ራሳቸውን በዚህ በትግል አቅጣጫ ማሰለፍ ያለባቸው። ወያኔ ከገባ ጀምሮ የተተከለው የጎሳ ፖለቲካ ሙሉ በሙሉ ተነቅሎ በሌላ እስካልተተካ ድረስ የአማራ ህዝብ ማንነትን መሰረት ያደረገ አደረጃጀት እና ትግል ሊጨናገፍ አይገባም። አይችልምም ! እንኳን ሳይፈርስ እና ቀጣዩ እና ሁሉን የሚያስማማው ስርአት ተደላድሎ ሳይተከል ቢተከልም የአማራ ብሄርተኝነት እንደከዚህ ቀደሙ ጨርሶ መጥፋት የለበትም። ከታሪክ መማር ያስፈልገናል። ዶክተር አብይ አህመድ ከምሁራኖች ጋር አደረጉት በተባለው ስብሰባ ላይ ”አሁን ያለው የፖለቲካ አደረጃጀት እና ፖሊሲ ይፈርሳል “አሉ ተብሎ በርካታ ሰዎች ጮቤ ረገጡ። የአማራን የማንነት አደረጃጀት እና ትግል መኮነን ጀመሩ። የሚገርመው ግን ሊፈርስ ይችላል እንጅ ፈረሰ አልተባለም። ህወሃት፣ኦነግ፣ኦህዴድ፣ኦዴግ፣ ሶዴፓ፣ ዴህዴን፣ኦፌኮ ሁሉም አሉ። ታዲያ የአማራን ህዝብ የህልውና ጥያቄ መልስ ለመስጠት የተጀመረው የአማራ ህዝብ አደረጃጀት እና ትግል ምን መልስ አግኝቶ ይቆማል ? ለምንስ ይኮነናል ? አዎ ! ይህ በፍፁም የሚታሰብ አይደለም። የአማራ ህዝብ ትግል ገና ያድጋል ይጎመራል። ህልውናውን ያስከብራል። ከራሱም አልፎ እንደሱ የዚህ ዘረኛ ስርአት ሰለባ ለሆኑት መከታ ይሆናል። ይህን አምነን ቀጥ ብለን እስካልቆምን እና የሚያዋጣውን መንገድ በፅናት እስካልተከተልን ድረስ ህልውናችንን የሚፈታተን ታዋቂ ሰው በመጣ ቁጥር እየተከተልን ወደመታረጃ ቦታችን በደስታ እንሄዳለን። የመርህ ህዝብ ከሆንን ዶክተር አብይ መጣ ፣ ዶክተር ብርሃኑ፣ አልያም ታማኝ በየነ አቋማችን እና የህልውናችን መሰረት የሆነውን መርሃችንን አስቀድመን እንወያያለን እንጅ በቀደዱልን ቦይ አንፈስም። ፈተናችን ገና ከፊት ነው። ሁሉም ጥግ ጥጉን ይዟል። አማራ ቀና እስካላለ ድረስ ማንም የህብረብሄራዊ አደረጃጀትን የሚቀበል ጎሳ የለም። ወደፊት አይኖርም አላልኩም። ግንቦት ሰባት የሚባል ድርጅት ከዶክተር አብይ መንግስት ጋር ተደራድሮ አገር ውስጥ ሊገባ እየተዘጋጀ ነው። ይህን ድርጅት የሚከተለው መርህ አልባ እና የትግል መስመሩ የጠፋበት ሰው ብቻ ነው። እኛም እንደህዝብ መስመሩ ጠፍቶብን ከሆነ መጥለፍ ሳይሆን መጠለፋችን እሙን ነው። ይህ ማለት ደግሞ የአማራን ህዝብ ትግል 50 ወደኋላ መለስነው ማለት ነው። ይህ በፍጹም መሆን የለበትም። በመርህ እና አዋጭ መስመር እንጅ በግለሰብ ዝና መነዳት የለብንም።

አማራ በጀመረው መስመር ነጻነቱን በቶሎ እውን ያደርጋል። ይህ እንደሚያዋጣ በተግባርም ታይቷል።

ራስ ሐመልማል

የአማራ ህዝብ ምድር ላይ መኖር ከጀመረ ጊዜ አንስቶ እስካሁን ድረስ እጅግ አስከፊ የሚባል ህይወትን እየገፋ ይገኛል። ድል ሲያደርግ ፣ ድሉን ሳያጣጥም ሌላ እንቅፋት ፊቱ ላይ ሲደቀን የመጣበትን መከራ ለማሸነፍ መላ ሲዘይድ ሲሞክር፣ ሲወድቅ ሲነሳ 21ኛው ክፍለ ዘመን ላይ ደርሷል። በዘመናዊ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ የአማራ ህዝብ የፖለቲካ አስኳል የአንድነት እና ሁሉን አሳታፊ ፖለቲካ አመለካከት ነበር። በዚህ አመለካከቱ ኢትዮጵያ የምትባል አንድት የተለያዩ ጎሳዎች የሚኖሩባት አገር ለመፍጠር ከፍተኛ መስዋእትነት ከፍሏል። እየከፈለም ይገኛል። ለበርካታ አመታት ባካሄደው ሁሉን አቀፍ የፖለቲካ አካሄድ ራሱን አጥቷል። አገር እመስርታለሁ ብሎ አማራነትን አዳክሟል፣ የአማራን እሴቶች አውድሟል፣ አማራን በኢኮኖሚ አድቅቋል። የመጨረሻ ድምር ውጤቱም ውድቀት በሚል ተደምድሟል። ከዚህ የተማሩ አንዳንድ የአማራ ልጆች…

Review Overview

User Rating: Be the first one !
x

Check Also

የአማራ ክልል ከፍተኛ የፀጥታ ክትትል ችግር አለበት – ሚኪ አማራ

⚡️ክልሉ እንደ ሃብታም ቤት ተበርግዶ (የሃብታም ቤትስ አንዳንዴ ይዘጋል) ሲፈልግ ከባድ መሳሪያ፤ ሲፈልግ ታንክ ፤ሲፈልግ ...