ስለ እኛ/ About Us

 

የግዮን ድምፅ መግቢያ

ዘላለማዊው የግዮን ወንዝ የብሔረ አማራ ማንነት ዓምድ ነው! ፍሰቱም የብሔረ አማራ እስትንፋስና የልብ ምት ነው። ግዮን ከብሔረ አማራ እትብት መብቀያ ከግዮን ተራሮች ፈልቆ ወደ ሱዳንና ግብፅ በመፍሰስ የግብፅ የደም ስር የሆነውን ታላቁን የናይል ወንዝ ይፈጥራል። ግዮን የገናና ስልጣኔ ባለቤት ከመሆን አልፎ ማሕበራዊ ጥበብንና ሳይንስን አበልፅጎ ለመላው ዓለም ያስረከበው የጥንታዊው ብሔረ አማራ ታላቅ ሕዝብነት ምልክት እና አምሳል ነው! የግዮን ምላት እና ርደት የስነፈለክ እና ስነቀመር እሳቤ መሰረት ነው። ግዮን የጥንት ጥቁር ግብፅ እና የጥንት ኢትዮጵያ ስልጣኔ መፍለቂያ የሆነውን የብሔረ አማራን ምድር ሲያለመልም እና ሲያበለፅግ የኖረ ሰማያዊ እና ምድራዊ ጅረት ነው። የታላላቅ ጠቢባን እና ባለግርማ ነገስታት መገኛ የሆነው የብሔረ አማራ ምድር፥ እና ዘላለምነትን በማይቆም ፍሰቱ ትዝብት አምቆ የያዘው ዘላለማዊው ምስጢራዊ ወንዝ ግዮን የማይነጣጠሉ አሐዶች ናቸው። ግዮን የብሔረ አማራ መፍለቂያ ምንጭ ነው። የተቀደሰው የግዮን ጠበል ፍሰት የብሔረ አማራ ጥንታዊ እና የተቀደሰ ማንነት ውሁድ አፅቅ ነው። የግዮን ወንዝ እና የግዮን ተራራዎችና አምባዎች ገናንነት የባሕርዩ የሆነው የብሔረ አማራ የማንነቱ ሕዋሶች ናቸው!

ግዮን የአማራ ሕዝብ ዘላለማዊ ልሳን ነው፥ በዚሁ አምሳል የግዮን ድምፅም የሕዝባችን የዘመኑ ልሳን ሆና ታጭታለች ። የግዮን ድምፅ በነፃ መርሕ የተዋጀች፥ ከብሔረ አማራ ሕዝባችን በስተቀር ለማንም የማትወግን የአማራ ሕዝብ ድምፅ ናት። የግዮን ድምፅ የገናናው የብሔረ አማራ ዘላለማዊ ነፃ ሕዝብነት እና ልዑላዊ ማንነት ተምሳሌት ናት። የግዮን ድምፅ በአማራ ሕዝባችን ፖለቲካዊ፥ ኤኮኖሚያዊ፥ ማሕበራዊ እና ባሕላዊ አኗኗር እና ሁኔታ ዙርያ የሚያጠነጥን የተሟላ፥ የተረጋገጠ እና ያልተበረዘ መረጃ ለማቅረብ ትተጋለች። ከዚህ ባሻገር ኢትዮጵያን፥ የአፍሪቃ ቀንድንና እንዲሁም ዓለማችነን የሚመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎችንም ታቀርባለች። የግዮን ድምፅ ዓቢይ ራዕይ በገዛ አገሩ ኢትዮጵያ በሰፈነው ጨቋኝ ፋሺስታዊ ስርዓት ወደር የሌለው ግፍ እና የመረጃ አፈና እየደረሰበት ላለውና ድምፁ ለታፈነው የአማራ ሕዝብ ድምፅ መሆን ነው። የግዮን ድምፅ በስደትም ሆነ በአገር ቤት የሚኖረውን መላውን ብሔረ አማራ ያለአንዳች የሃይማኖት፥ የፖለቲካ አመለካከት ወይም ሌላ የልዩነት ምክንያት በአንድ ግዮናዊነት ርዕዮት እና በአንድ ብሔረ አማራ ሕዝብነት ለማስተሳሰርና የኖረ የማይሻር አንድነቱን ለማበልፀግ ትተጋለች። የግዮን ድምፅ የቦርድ አባላት፥ ሰራተኞች እና በጎ ፈቃደኞች የሰው ልጅ ነፃነትን እና ክብር የሚያስቀድሙ እሴቶችን ይጠነቅቃሉ፥ ያከብራሉ። የብሔረ አማራንም ሆነ የመላውን የሰው ልጅ በነፃ የማሰብ እና መረጃ የማግኘት ሰብዓዊ መብቶችንም ባላሰለሰ ታማኝነት ይጠብቃሉ። የግዮን ድምፅ መዳረሻ ግብ ጠንካራ፥ ምሉዕ እና የማይበገር አማራዊ ሃልዮት እና ማንነት ማስረፅ እና መገንባት ነው።

የግዮን ድምፅ ተልዕኮ በኢትዮጵያ እና በዓለም ዙርያ የሚገኘውን ብሔረ አማራ የሚመለከቱ ነፃ፥ የተጣሩ እና ፋይዳ ያላቸው ዜናዎች እና ሌሎች መረጃዎችን ለሕዝባችን ማቅረብ ነው። ከዚሁ ጎን ለጎን የከበረውን የብሔረ አማራ ጥንታዊ ቋንቋ፥ የተቀደሰ ባሕል ዕና ንዑድ ታሪክ የመንከባከብ፥ የማሳደግ እና የማበልፀግ ትውልዳዊ ሃላፊነታችነን እናስቀድማለን። መላው ተልዕኳችን እና ተግባራዊ እንቅሳቃሴያችን ዛሬ በገጠመው ፈተና ሕልውናው እና ማንነቱ አደጋ ላይ የወደቀው ብሔረ አማራ ሕዝባችን ሕልውናውን እና ታላቅ ሕዝብነቱን ለማረጋገጥ ከሚያደርገው የሞት ሽረት ትግል ጋር በፅኑዕ የተቆራኘ ነው።

የግዮን ድምፅ በዓለም ዙርያ ለሚገኘው ብሔረ አማራ ሕዝባችን አስተማማኝ እና በቀላሉ ተደራሽ የሆነ የመረጃ ምንጭ እንድትሆን ማስቻል ቀዳሚ ግባችን ነው። ጠቃሚ መረጃዎችን ብሎም ትምሕርታዊ፥ አዝናኝ፥አነሳሽ እና አጎልባች መርሐግብሮችን ለመላው ብሔረ አማራ ሕዝባችን ለማድረስ እንተጋለን። በአካባቢያዊ፥ ሐገራዊ እና ዓለም ዓቀፋዊ ደረጃ የተደራጁ ፥የተሰናዱ እና የተናበቡ ምሉዕ መረጃዎችን ለሕዝባችን ማድረስ፥ በዋናነት በግዮን ምድሩ የሚኖረውን ብሔረ አማራ ሕዝባችነን ማዕከል ያደረጉ  እንደፍላጎቱ የተመጠኑ መርሐግብሮችን ማሰናዳት እና ተደራሽ ማድረግ የዘወትር ጥማታችን ነው። በተጨማሪም አሁን በኢትዮጵያ ባለው ሰው በላ የፋሺስት አገዛዝ በአማራ ሕዝባችን ላይ እያደረሰ ያለውን ግፍና መከራ ብሎም በዚሁ አገዛዝ በአማራ ሕዝብ ላይ እየተፌፀመ ያለውን ያልተለቀሰለት የዘር ማጥፋት ድርጊት (ጄኖሳይድ) ለዓለም ሕዝብ ለማሳወቅ አበክረን እንሰራለን።

የግዮን ድምፅ የመላው ብሔረ አማራ መድረክ ናት። በዓለም ዙርያ የሚገኙ አማራዎችን በሙሉ የማስተማር፥ የማዝናናት እና የማበልፀግ ተግባራትን እናከናውናለን። የአማራ ሕዝባችን ያልተጓደለ ነፃነት እና ክብር የሚቀዳጅበትን ሁኔታ ለማመቻቸት የሚረዱ ተግባራትን ያላንዳች ማሰለስ እንተገብራለን፥ ለሕዝባችን ልማት እና ብልፅግና የሚበጁ ጥረቶችን ያለመታከት እናደርጋለን። ለብሔረ አማራ ሕዝባችን ችግሮች በራሱ በስልጡን ነፃ ሕዝባችን ማንነት፥ ትውፊት እና እሴቶች ላይ የተመሰረቱ ሕዝብ አክባሪ እና አስቀዳሚ መፍትሔዎችን ለማስለጥ የሚረዱ የሃሳብ ልውውጦች እንዲበራቱ እንተጋለን። በምንከውናቸው ተግባራት ሁሉ በፍፁም ለድርድር ለማናቀርበው ለብሔረ አማራ ሕዝባችን ሕልውና፥ ማንነት እና ነፃ ሕዝብነት የማይለወጥ ቅድምና እንሰጣለን። በተጨማሪም የመላው የሰው ልጆችን የነፃነት፥ ፍትሕ እና የሰው ልጅ ባሕርያዊ ክቡርነት እሴቶችን እናከብራለን፥ እናሳድጋለን። የብሔረ አማራን ገናና ታሪክ እና የሕዝብነት ክብር ከማናቸውም ጥቃት በቅንዓት እንከላከላለን። ስለገናናው የአማራ ሕዝብ ጊዜ የማይሽራቸው እውነቶችን ለመረዳት ወደግዮን ይምጡ። የግዮን ድምፅ በጥንታዊው ጊዜ አይሽሬ የግዮናዊው አማራ የተቀደሰ ትውፊት መሰረት ወደደጇ የሚመጡትን ሁሉ በፍቅር እና በአክብሮት ትቀበላለች! በአማራነት ግዮናዊ ቆባ አምሳል የአማራ ሕዝብ አንደበት ወደሆነችው የግዮን ድምፅ እንኳን ደህና መጡ!

~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~

Introduction

Eternal Gihon is the Pillar of Amhara Identity! Its Flow is the Heartbeat of the Amhara Nation! Originating from the Heart of Amhara Land, Gihon flows into the Sudan and Egypt to become the Great Nile-the Life Blood of Egypt. Gihon is the Living Symbol of the Glory of Ancient Amhara-a Great Civilized People that gave to the world the arts and the sciences. The ebb and flow of the Gihon underlies the birth of Astronomy and Mathematics. It nurtures and edifies the Land of the Amhara-an Ancient, Proud and Fiercely Independent People that created the ancient civilization of Ancient Ethiopia and Ancient Egypt! Amhara Land-the Land of Great Sages and Majestic Kings-is synonymous with Gihon-the Eternal Mystic River, the Seer and Witness of All Eternity. Gihon is the Fountain of the Amhara People! The Identity of the Amhara is as Ancient as, and Indelibly intertwined with, the Timeless flow of the Sacred River-Gihon!
As Gihon is the Eternal Voice of the Amhara, Gihon Media Center is the Temporal Voice of our people. Gihon Media Center (GMC) is an independent voice of the Amhara People. It represents the Eternal Free Spirit and Identity of our Amhara People. It strives to provide full, unadulterated and well-verified information about the political, economic, social and cultural life of the Amhara People. It also disseminates credible information about Ethiopia, the Horn of Africa and the World. Its main vision is to serve as the Voice of the Voiceless Amhara People that have been denied access to their own media outlets by the oppressive regime in Ethiopia. It seeks to unite all Amhara, at home and in the diaspora, irrespective of their religion, political opinion and other differentiating factors. The Board, Staff and volunteers of GMC are committed to the values of human freedom and dignity. They have an unwavering commitment to Freedom of Thought, Expression and Information. Their ultimate goal is to enhance a strong, comprehensive and thriving Amhara Consciousness and Identity.

Our Mission is to gather, process and disseminate independent, verified and focused news and other information about, and for, the Amhara people in Ethiopia and across the globe. In doing so we strive to preserve and promote our Ancient Language, Sacred Culture, Venerated History and Enduring Values. In all our activities, we focus on promoting social and economic justice, equality and human freedom. Our mission is singularly tied to the aspiration to ensure the survival and greatness of the Amhara People amidst the enormous challenges our people is facing currently.

Our Goal is to make GMC an accessible and dependable source of information for our people throughout the world. We do our best to provide news and entertainment services as well as useful educational and inspirational programs for our people. We strive to present all-rounded information to our audience in the form of locally created programming, other community station programming and other nationally syndicated programs. We work hard to inform the world to know about the woeful sufferings of our Amhara People under the current regime, including the “Silent Genocide” on the Amhara People that has been persistently going on for more than a quarter of a century.
GMC is a forum for all Amhara. We inform, educate and entertain Amhara all over the world. We work for the advancement, development and full-fledged freedom and dignity of our Amhara People. We foster the values of freedom, justice and human dignity through all our undertakings. We defend the history and dignity of the Amhara. Come to Gihon to be enlightened about the timeless truth of the Amhara People. Gihon Media Center welcomes all as is the Ancient Sacred Tradition of the Amhara People-the People of Gihon!