ዳግማዊ ላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ሆኑ

ዳግማዊ ላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ሆኑ።

አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሰሜን ወሎ ዞን በዋድላ ወረዳ ጋሸና ከተማ አካባቢ ከአለት ተፈልፍለው የተሰሩት ዳግማዊ ላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል።በዳግማዊ ላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያን አራት ፍልፍል ቤተ መቅደሶች ናቸው ተጠናቀው ለአገልግሎት ከፍት የተደረጉት።
ውቅር አብያተ ክርስቲያናቱ ግንበታ በ2003 ዓ.ም የተጀመረ ሲሆን፥ በያዝነው ወር ተጠናቀው ለአገልግሎት ክፍት መደረጋቸው ተገልጿል። ውቅር አብያተ ክርስቲያናቱን የገነቡት በአባ ገብረ መስቀል ተሰማ፥ “ሁሉም የሆነው በፈጣሪ ፈቃድ ነው” ይላሉ።
እስካሁን አራት ቤተ መቅደሶች ተሰርተዋል ያሉት አባ ገብረመስቀል፥ “በቀጣይም እንደ እግዚአብሄር ፍቃድ ውቅር አብያተ ክርስትያናቱን ስራ በሌሎች አካባቢዎችም ለመቀጠል አስበናል” ብለዋል።
የግንባታ መሳሪያዎቹ ሙሉ በሙሉ ባህላዊ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ውቅር አብያተ ክርስቲያናቱ የሰሜን ወሎ ዞን ሀገረ ስብከት ረዳት ጳጳስ በፁእ አቡነ ኤርሚያስ፣ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል የተወጣጡ እና የዋድላ አካባቢ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ በተገኙበት መመረቁን ከአማራ መገናኛ ብዙሃን ድርጅት ያመገኘው መረጃ ያመለክታል።

Print Friendly, PDF & Email