ፅሁፎች

የአብን ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ በተለያዩ ሚዲያዎች ያደረጉትን ቆይታ ግምገማ | በ መልካሙ ተሾመ

የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ ( አብን) ቃል አቀባይ የሆኑት አቶ ክርስቲያን ታደለ ለአገር ቤቱ ሪፖርተር ጋዜጣ እና ለቢ.ቢ.ሲ የአማርኛ የፌስቡክ ገጽ የሰጡትን ቃለ ምልልስ በጥሞና ተመለከትኩ፡፡ ይህን ተከትሎ የማይናቁ ትችቶች ተሰጥተዋል፡፡ በዚህ ጽሁፍ በዚሁ ጉዳይ ላይ ጥቂት ነጥቦችን ብቻ እንዳስሳለን፡፡ 1)የአማራ ታሪካዊ ግዛቶች በጠቅላላ አነጋገር ኃላፊው ጥያቄዎችን ያብራሩበት ጥንቃቄ እና ብስለት የሚደነቅ ነው፡፡ ታሪካዊ ግዛቶች የሚሏቸው እነማን እንደሆኑ በተደጋጋሚ ሲጠየቁ በሃቅ ...

Read More »

ሕዝባዊና ግዛታዊ አንድነቱ በመገሰሱ ምክንያት የአማራ ሕዝብ ህልውና አደጋ ውስጥ ነው ብለን እናምናለን | ክርስቲያን ታደለ

አቶ ክርስቲያን ታደለ፣ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ከሪፖርተር ጋዜጣ ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስ  በቅርቡ የመመሥረቻ ጉባዔውን ያካሄደው የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ፓርቲ በይፋ መመሥረቱ ለደጋፊዎቹና ለአባላቱ ግልጽ አድርጓል፡፡ ከሳምንት በፊት በአማራ ክልል ርዕሰ ከተማ በሆነችው በባህር ዳር ከተማ መመሥረቱን ይፋ ያደረገው ፓርቲው በሙሉ ዓለም የባህል አዳራሽ ለአባላቱና ለደጋፊዎቹ ወደ ኢትዮጵያ የፖለቲካ መድረክ መግባቱን ገልጿል፡፡ ፓርቲው በዋናነት ከተለያዩ ...

Read More »

የ ዐማራ ብሔራዊ ንቅናቄ መመሥረትን አስመልክቶ | በአቶ አንዱዓለምተፈራ

ቅዳሜ፣ ሰኔ ፪ ቀን፣ ፳ ፻ ፲ ዓመተ ምህረት በፖለቲካ ዓለም፤ አዲስ ነገር ሲከሰት፤ በጥርጣሬ ዓይን መመልከቱ የተለመደ ነው። በተለይም የራሳቸው ድርጅት ያላቸው ግለሰቦች፤ ክስተቱን ከግለሰብ ማንነታቸው በተጨማሪ፤ በድርጅታቸው መነፀር ስለሚመለከቱት፤ የመጀመሪያ ግንዛቤያቸው፤ ይህ ክስተት፤ ለኔ እናም ለድርጅቴ፤ ይጠቅመናል? ወይንስ ይጎዳናል? ለዚህስ መልሳችን ምንድን ነው? ከሚል ስለሚነሱ፤ በጎ ፈቃደኝነታቸው ልጓም አለው። ይህ አመለካከት ደግሞ፤ ሁሉን ነገር ያሸወርረዋል። እውነትና ሐሰት፣ እኛና ...

Read More »

ሃውጃኖ- የራያው መብረቅ | ለግዮን መገናኛ ብዙኃን የተላከ

ሃውጃኖ- የራያው መብረቅ ከጥንት ጀምሮ ስለ ራያ ማንነት ሲብሰለሰል እና ሲታገል ስለተሰዋው ይርጋ አበበ፤ በትግል ስሙ ሃውጃኖ ከህግ ባለሙያው እና ገጣሚ መንግስቱ ዘገየ ጋር በስልክ ስናወጋ፤ የሃውጃኖ ታሪክ ለህዝብ ይደርስ ዘንድ ወደ መጽሃፍ ለመቀየር ስናስብ ‘’ሃውጃኖ የራያው መብረቅ’’ እሚል ገላጭ መጽሃፍ እንጽፋለን ብሎ ወኔ አላበሰኝ፡፡ እኔም ለዚች አጭር ጽሁፍ የእርሱን ቃል ተውሸ ልጠቀምባት አሰብኩ፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው፤ ሰሞኑን ለእረጅም ዓምታት ...

Read More »

እኔማ ከልቤ ነበር የመከርኩት፡፡መሬት እና ሃብት የግለሰቦች ይሁን…. | የሽሀሳብ አበራ

“እኔማ ከልቤ ነበር የመከርኩት፡፡መሬት እና ሃብት የግለሰቦች ይሁን፡፡መሬት የመንግስት ሳይሆን የግለሰቦች ፀጋ ይሁን ብየ ደጋግሜ ነገርኩት” አቶ መለስ ግን” ሃብት በግለሰብ ከሆነ መሬት በሙሉ በአማራው እጅ ይያዛል፡፡ብዙ ሃምታሞች አማራ ስለሆኑ መሬት በመንግስት ቁጥጥር አድርገን የሃገሪቱን ምጣኔ እናስተካክላለን::” አለኝ ይላሉ ኸርማን ኮህን፡፡ … 1970 ዎቹ መጨረሻ ጀምሮ ታላቋ ሩሲያ እየተቀዛቀዘች፣አሜሪካ እየገነነች ስትመጣ የአሜሪካ የካፒታሊዝም ገበያ እና የሊብራል ዲሞክራሲ ገበያው ተፋፋመ፡፡ … ...

Read More »

አማራን በዘላቂነት የመቀራመት ሴራ | ዴቭ ዳዊት

ዩ.ኤስ. አሜሪካ የፖለቲካ ስልጣን ታሪክ ውስጥ እንደኖሩበት ዘመን ተፅዕኗቸው ቢለያየም የሩዝቬልት፣የኬኔዲ አልያም የቡሽ ቤተሰቦች በመጀመሪያው ረድፍ የሚገኙ ተፅዕኖ ፈጣሪ እና በአለም ፖለቲካ ላይ አሻራቸውን ያኖሩ ሊባል ይችላል። ይሁን እንጂ ገና በ19ኛው ክፍለ ዘመን መባቻ ላይ የአሜሪካ ካፒታሊታዊ ስርዓት ከድንበሩ ተሻግሮ ወደ እነ ሀዋይ ደሴት መፍሰስ ሲጀምር ፥ ብሎም እየጠቀለለ የራሱ አካል ማድረግ ሲጀምር በካፒታሊስቱ እና በፖለቲከኛው መካከል የጥቅም መስተጋብርን የሚፈጥር ...

Read More »

የአንዳርጋቸውም ሆነ የመሰል እስረኞች መፈታት አማራን ከጥፋት አይታደገውም | ከግዮን አምደኛ

አንዳርጋቸው እንኳንም ተፈታ። ሌሎቹም ይፈቱ። ሆኖም የታሰሩት በአማራው ምክንያት አልነበረም እና መፈታታቸው አማራን ከጥፋት አይታደገውም። ለአማራ ህልውና የሚደረገውን የትግል አቅጣጫም አይቀለብሰውም። ተያያዥነት ያለው ነገር አይደለም። የአማራ ትግል አንዳርጋቸውን አስፈትቶቷል እንጅ አንዳርጋቸው አማራን ለመታደግ ታግሎ አያውቅም። ዛሬም አንዳርጋቸው ሲፈታም ድሮም ሳይፈታም አማራን የሚያስገድለው ህግ አለ፣ ነበረም። አማራን የሚያፈናቅለው ፣ ሀገር አልባ ያደረገው ህግ ዛሬም አለ። ጸረ አማራውን ህግ መሰረት አድርገው ሲያፈናቅሉ፣ ...

Read More »

ፕራይቬታይዜሽን (ግለ-ምጣኔ ኃብት ?) | ከፌስቡክ የተገኘ

ህወሃት የፖለቲካውን መድረክ ስትቀማ የኢኮኖሚ የበላይነቱን ላለማጣት የዘየደችው ሴራ እንደሚታወቀው ህወሃት ስልጣን ከጨበጠ ጊዜ ጀምሮ የምእራቡ አለም የህወሃት ደጋፊዎች በኢትዮጵያ ግለ ኢኮሚኖሚ እንዲጀመር ከፍተኛ ግፊት ሲያደርጉ ነበር። ምክንያቱም በምእራቡ አለም ተወዳዳሪ መሆን ያልቻሉ በርካታ የነጭ ባለሃብቶች እና ተቋማት በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በቀላሉ ሃብት ማካበት ይችሉ ስለነበር ነው። ሆኖም ፖለቲካ ኢኮኖሚ የነበረበት ጊዜ እና ፖለቲካውንም ኢኮኖሚውን በብቸኝነት የተቆጣጠረችው ትህነግ-ህወሃትስለነበረች መለስ ዜናዊ በአንገቴ ...

Read More »

አማራ ፖለቲካ ተግዳሮቶችና መፍትሄወቻቸዉ ባጭሩ | ከግዮን አምደኛ

አማራ በኢትዮጲያ ፖለቲካ ባለፉት ስልሳ አመታት በተለያዩ ህብረብሄራዊ ድርጅቶች ከጅምሩ ተሳትፎዉ ቀላል እንዳልነበር ይታወቃል፡፡ በጊዜዉ በፀረአማራነትና በበታችነት ስሜት ተነሳስተዉ እነ ህግደፍ/ሻቢያ፣ህወሃትና ኦነግን የመሳሰሉ ድርጅቶች ሲመሰረቱ አማራ ያኔ በራሱ ተደራጅቶ ቢሆን ኖሮ አሁን አለንበት ችግር ላይ ባልወደቅን ነበር፡፡አማራዎች ባለፈዉ ከግማሽ ክ/ዘመን በላይ የተሳተፉባቸዉን የፖለቲካ አሳለፍ(ከመንግስት መዋቅር ዉጭ ያሉትን) ባጭሩ በሶስት ከፍሎ ማየት ይቻላል፡፡ የመጀመሪያዉ ምዕራፍ የስልሳዎቹ እና ከዚያም በኋላ የመጣዉ አማራዎች ...

Read More »

መክት አማራ

ትግሬ ህወሃትሥልጣን ከተቆናጠጠበት ጊዜ ጀምሮ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች በተለይም ከ”ኦሮሚያ እና ከቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል” የተፈናቀሉ አማራዎች ቁጥር እጅግ ከፍተኛ ነው። በዚህ ዙሪያ ዝርዝር ምረጃ ለማግኘት ኢሰመጉ ያወጣቸውን በርካታ መግለጫዎች ማገላበጥ ይቻላል። ይህ ችግር መፍትሔ ሳያገኝ እየተባባሰ አሥርት አመታቶች ተቆጠሩ። ኢሰመጉ ከ 1985 ዓ.ም ጀምሮ በየጊዜው ካወጣቸው መግለጫዎች ጥቂቱን ኢሰመጉ1 ፣ ኢሰመጉ2 ፣ ኢሰመጉ3 ፣ ኢሰመጉ4 መመልከት ይቻላል። የአማራ ህዝብ ላይ ...

Read More »

ከባሮን ሮማን ፖርቹስካ እስከ ዋለልኝ መኮንን፣ከዋለልኝ እስከ ታምራት ላይኔ | የሺሃሳብ አበራ

 … ባሮን ሮማን ከ 19 20 ዎቹ መጀመሪያ እስከ 1926 ዓም አዲስ አበባ ለነጮች ጠበቃነት ሲሰራ የቆየ አውሮፓዊ ነው፡፡ባሮን አብሲኒያ የባሩድ በርሚል ብሎ ባወጣው ባለ 91 ገፅ ሰነድ አውሮፓ ኢትዮጲያን ቅኝ ለመግዛት ማድረግ ስላለባቸው ጉዳዮች ይተነትናል፡፡በመጀመሪያ የዳግማዊ ምኒሊክ አልጋ ወራሽ የሆኑት ቀዳማዊ ሃይለስላሴ ነጭን እንደሚጠሉ ከማሳያዎች ጋር ያቀርባል፡፡የተባበሩት መንግስት ድርጅት ማህበር ጥቁሪቷ ሃገር ኢትዮጲያ አባል መሆን እንዳልነበረባት ይወተውታል፡፡ ኢትዮጲያን ለማዳከሞ ...

Read More »

አቸናፊዎች ታሪክን ይጽፋሉ | አንዱዓለም ተፈራ

አርብ፤ ግንቦት ፲ ፯ ቀን ፳ ፻ ፲ ዓመተ ምህረት ( 5/25/2018 ) ( ሆኖም፤ በጉልበት ለያዙት በትረ ሥልጣን እንጂ፤ ለሚጽፉት ታሪክ፤ የእውነታው ባለቤትነት የላቸውም። ) ታሪክ ሲጻፍ፤ የነበረውን መተረኩ፤ በሁለት መንገድ ይኬድበታል። አንደኛው የነበረውን እንዳለ ማቅረብ ነው። ሌላው ደግሞ፤ ላደረጉት ተግባር ማረጋገጫና ማስመከሪያ ለማድረግ፤ የተግባሩን ትክክለኝነት ለማስረገጥ፤ ወደሚፈልጉት አቅጣጫ አንጋዶ ማቅረብ ነው። ይህ ሁለተኛው ሂደት፤ ራስን ለማሞካሸትና ሌሎችን ለማንቋሸሽ፤ ...

Read More »

አማራውና እና የብሄር ፌደራሊዝሙ | የሺሀሳብ አበራ

ዮሃንስ ለታ አዲስ አበባ ገቡ፡፡መግባት ነበረባቸው፡፡የምስራቅ አፍሪካው የአሜሪካ የደህንነት ሹም ኸርማን ኮህንን በ 1982 ዓም በኢትዮጵያ ላይ ካደራደራቸው ሶስት ሰዎች መካከል ዮሃንስ አንዱ ናቸው፡፡ኢሳያስ እና መለስም ደግሞ ሌሎቹ፡፡፡ … ሶስቱም በወቅቱ ኢትዮጲያን የሚረዱበት መንገድ ተመሳሳይ ነው፡፡ዛሬም ብዙ አይለያይም፡፡ለሶስቱም ኢትዮጲያ ቅኝ ገዥ በመሆኗ ነፃ ለመውጣት እና ሃገር ለመመስረት ታግለዋል፡፡ ኢሳያስ ኤርትራን ሃገር አደረጉ፡፡አቶ መለስ የኢትዮጵያ ፖለቲካ በእጃቸው ስለገባላቸው በ 1982 ከትግራይ ...

Read More »

የዐማራ ብሔርተኝነት ሀ፣ ሁ ( ላልተረዱት ) | አንዱዓለም ተፈራ

ሰኞ፣ ግንቦት ፮ ቀን ፳፻፲ ዓመተ ምህረት የዐማራ ብሔርተኝነት፤ በተለምዶ ከተረዳናቸው ብሔርተኝነቶች የተለዬ ነው። የዐማራ ብሔርተኝነት፤ የዐማራውን የበላይነት በሌሎች ላይ ለመጫን የተነሳ አይደለም። የዐማራ ብሔርተኝነት፤ ይሄ ወይንም ያ ጎደለብኝ ብሎ የተነሳ አይደለም።ዐማራ፤ ዐማራነቱን ለኢትዮጵያዊነት አስረክቦ፤ ኢትዮጵያዊ ነኝ! ብሎ፤ ይሄን ኢትዮጵያዊነት፤ ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ጋር በመጋራት፤ ለዘመናት በአንድነት ኖሯል። ከረጅሙ ታሪካችን አኳያ፤ በጣም አጭር፣ እጅግ በጣም አጭር በሆነ ጊዜ ውስጥ፤ በቁጥር ፵ ...

Read More »

ተጋድሏችን ፍልስፍናዊ ነው ወይስ መረጃዊ ነው? | ዐምዴ ጽዮን ዘአክቲሳኒስ

 “ስለዚህም ማስረጃው ለምን መጣ የሚል ተከራካሪ ሳይሆን የቀረበውን ማስረጃ መሰረት አድርጎ ተጋድሎውን ቅርፅ የሚያስይዝ እና ለግብ የሚያበቃ አስተሳሰብ ያስፈልጋል” የአማራን ተጋድሎ ብዙዎች እንደስጋት ስለሚያስቡ ( ሀሰት ቢሆንም) ለሰርጎ ገብነት የተጋለጠ ነው። እንደማንኛውም የትግል ሂደት የአማራ ተጋድሎ የጀመረው ማንነትን መሰረት ባደረገ በንጹሕ ፍልስፍና ነው። ያም ማለት በመጀመርያ ራስን በማወቅ ላይ የተመሰረተ የትግል ሂደት ነው። ራስን በማወቅ ሂደት ሁለት አበይት ፈተናዎች አጋጥመዋል ...

Read More »